La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 9:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህንንም ሁሉ ለኢዩ በነገሩት ጊዜ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “ይህ ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በአገልጋዩ ቴስቢያዊው በኤልያስ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው፤ ይኸውም ‘የኤልዛቤልም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ተመልሰውም ይህን ሲነግሩት፣ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ለባሪያው ለቴስብያዊው ለኤልያስ፣ በኢይዝራኤል ምድር ዕርሻ ውስጥ ውሾች የኤልዛቤልን ሥጋ ይበሉታል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህንንም ሁሉ ለኢዩ በነገሩት ጊዜ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “ይህ ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በአገልጋዩ ቴስቢያዊው በኤልያስ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው፤ ይኸውም ‘የኤልዛቤልም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ተመ​ል​ሰ​ውም ለኢዩ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም፥ “በባ​ሪ​ያው በቴ​ስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ እጅ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ የኤ​ል​ዛ​ቤ​ልን ሥጋ ውሾች ይበ​ላሉ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ተመልሰውም ነገሩት፤ እርሱም “በባሪያው በቴስብያዊ ኤልያስ ‘በኢይዝራኤል እርሻ የኤልዛቤልን ሥጋ ውሾች ይበላሉ፤

Ver Capítulo



2 ነገሥት 9:36
9 Referencias Cruzadas  

“ይዲድያ” የሚል ስም እንዲያወጣለት ነቢዩ ናታንን አዘዘው፤ ይህም “በእግዚአብሔር የተወደደ” ማለት ነው።


ስለ ኤልዛቤልም እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ ሬሳዋን በኢይዝራኤል ከተማ ውስጥ ውሾች ይበሉታል፤


እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረውም ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፤ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ እግር ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ፤ ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር።


ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።


በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር ለንጉሥ ኢዩ “ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ በእስራኤል ይነግሣሉ” ሲል የተናገረው የተስፋ ቃል ተፈጸመ።


ኤልዛቤል የመቀበር ዕድል እንኳ አታገኝም፤ የእርስዋም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤’ ” ይህን ሁሉ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወጣቱ ነቢይ በሩን በመክፈት ከዚያ ክፍል ወጥቶ ሸሸ።


ሊቀብሩአት የሄዱ ሰዎች ግን ከራስ ቅልዋ፥ ከእግሮችዋና ከእጆችዋ አጥንት በቀር ምንም አላገኙም፤


አሮንና ልጆቹም በሙሴ አማካይነት እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ፈጸሙ።


ኢይዝራኤል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖሐ፥