“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤
2 ነገሥት 24:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተለይም ምናሴ የንጹሓን ሰዎችን ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓን ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ንጹሕ ደም ስላፈሰሰ ነው። ኢየሩሳሌምም በንጹሕ ደም እንድትጥለቀለቅ በማድረጉ፤ እግዚአብሔር ይቅርታ ለማድረግ አልፈለገም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተለይም ምናሴ የንጹሓን ሰዎችን ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓን ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቁንም ስለ ገደለ ኢየሩሳሌምንም በንጹሕ ደም ስለ ሞላ እግዚአብሔር ይራራ ዘንድ አልወደደም። |
“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤
ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።
ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቊጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።
እነርሱ ለከነዓን ጣዖቶች መሥዋዕት አድርገው ያቀረቡአቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በመግደል ንጹሕ ደም አፍስሰዋል፤ ምድሪቱም በደም ረከሰች።
የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን በኢየሩሳሌም ስለ ፈጸመው ክፋት ሁሉ በእነርሱ ላይ ከሚደርሰው ነገር የተነሣ የዓለም ሕዝብ እንዲሠቀቅ አደርጋለሁ።”
ይህንንም የማደርገው ሕዝቡ እኔን ስለ ተዉና ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ ይህን ስፍራ ስላረከሱ ነው፤ እነርሱም ሆኑ የቀድሞ አባቶቻቸው ከይሁዳ ነገሥታት ጭምር ስለ ነዚህ አማልክት የሚያውቁት ነገር የለም፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ንጹሖች ሰዎችን በመግደል ይህ ስፍራ በደም የተሞላ እንዲሆን አድርገውታል።
ልብሶችሽ በንጹሖችና በድኾች ደም ተበክለዋል። “ነገር ግን ይህን ሁሉ አድርገሽ፥ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በእርግጥ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አይቈጣም!’ ትያለሽ፤ ነገር ግን ‘እኔ ኃጢአት አልሠራሁም’ ብለሽ በመካድሽ ምክንያት እኔ እግዚአብሔር እፈርድብሻለሁ።
ለከተማይቱ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፦ በውስጥሽ ያሉትን ብዙዎችን ስለ ገደልሽና ጣዖቶችን በማምለክ ራስሽን ስላረከስሽ እንድትጠፊ የተወሰነበት ጊዜ ተቃርቦአል።
ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ለነፍሰ ገዳዮች ከተማ ወዮላት! ከዝገቱ እንዳልጠራና ከቶም እንደማይጠራ ብረት ድስት ሆናለች፤ በውስጥዋ ያለውን ቊራጭ ሥጋ ሳትመርጥ አንድ በአንድ አውጣው።
“እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ሥጋ ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ጣዖት ታመልካላችሁ፤ ግድያ ትፈጽማላችሁ፤ ታዲያ፥ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ እንዴት ምድሪቱ የእኛ ርስት ናት ትላላችሁ?
ይህን ብታደርጉ የምትኖሩበትን ምድር ታረክሳላችሁ፤ የነፍስ ግድያ ወንጀል ምድሪቱን ያረክሳል፤ ስለዚህ የነፍሰ ገዳዩ ደም ካልፈሰሰ በቀር ምድሪቱን ከደም ለማንጻት የሚፈጸም ሌላ ሥርዓት የለም።
ይህንንም የምታደርገው እግዚአብሔር አምላክህ እንድትኖርባት ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ንጹሕ ደም እንዳይፈስስና አንተም የደሙ ተጠያቂ እንዳትሆን ነው።
እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን ርግማን ቃላት ሰምቶ ምንም እንኳ በራሴ መንገድ ብቀጥል እኔ እድናለሁ ብሎ በልቡ ቢያስብ በደጎችና በክፉዎች ሰዎች ላይ ጥፋትን ያመጣል።