2 ነገሥት 14:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሜስያስ “የጨው ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላዕ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጨው ሸለቆ በተባለው ቦታ ዐሥር ሺሕ ኤዶማውያንን ድል ያደረገ፣ ሴላን በጦርነት የያዘና እስከ ዛሬም ድረስ ዮቅትኤል ተብላ የምትጠራበትን ስም ያወጣላት አሜስያስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሜስያስ “የጨው ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላዕ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በጨው ሸለቆ ከኤዶምያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላንም በጦርነት ወስዶ ስምዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም በጨው ሸለቆ ከኤዶምያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላን በሰልፍ ወስዶ ስምዋን እስከ ዛሬ ድረስ ዮቅትኤል ብሎ ጠራት። |
በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።
አሜስያስ ሆይ! እነሆ፥ አንተም ኤዶማውያንን ድል ስላደረግህ ልብህ በትዕቢት ተሞልቶአል፤ በአገኘኸውም ድል በመደሰት ዐርፈህ በቤትህ ብትቀመጥ ይሻልሃል፤ በአንተና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍትን የሚያስከትል ነገር ለመቈስቈስ ስለምን ትፈልጋለህ?”
አለታማው ገደል ላይ የምትኖሪ፥ እስከ ተራራማው ጫፍ ድረስ የምትደርሽ ሆይ! ተፈሪነትሽና የልብሽ ኲራት አታለውሻል፤ ምንም እንኳ መኖሪያሽን እንደ ንስር ጎጆ ብታደርጊ እኔ ከዚያ ላይ አወርድሻለሁ ይላል እግዚአብሔር።”
የልብህ ትዕቢት አታሎሃል፤ በጠንካራ አለት በተመሸገ ከተማ ውስጥ ትኖራለህ፤ የምታድርበትም ቤት በከፍተኞች ተራራዎች ላይ የተሠራ ነው፤ ‘ካለሁበት ስፍራ ማን ሊያወርደኝ ይችላል?’ በማለት ትመካለህ።