ስለዚህ እባክህ ይህን ያቀረብኩልህን ስጦታ ተቀበለኝ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ሰጥቶኛል” አለ። ስጦታውን እንዲቀበለው ያዕቆብ ዔሳውን አጥብቆ ለመነው። እርሱም ተቀበለው።
2 ቆሮንቶስ 9:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ልትሰጡ ቃል የገባችሁበትን የልግሥና ስጦታችሁ በቅድሚያ እንድታዘጋጁ እንዲያስታውሱአችሁ በማለት እነዚህ ወንድሞች ከእኔ ቀድመው ወደ እናንተ እንዲመጡ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ በዚህ ዐይነት እኔ በምመጣበት ጊዜ የልግሥና ስጦታችሁ ዝግጁ ይሆናል፤ እናንተም የምትሰጡት በግድ ሳይሆን በፈቃደኛነት መሆኑን ያሳያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ እንዲመጡና ከዚህ በፊት ለመስጠት ቃል የገባችሁትን ስጦታ አጠናቅቃችሁ እንድትጠብቋቸው፣ እነርሱን መለመን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቻለሁ፤ እንግዲህ በልግስና ለመስጠት ያሰባችሁት ነገር በግዴታ ሳይሆን በፈቃደኝነት የተዘጋጀ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ዝግጁ እንድትሆኑ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን የልግስና ስጦታ እንደ ግዴታ ሳይሆን በበጎ ፈቃደኝነት ቀደም ብለው እንዲያዘጋጁ፥ እነርሱን መለመን አስፈላጊ መሆኑን አስቤበታለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው በቅድሚያ የተናገራችኋትን በረከታችሁን እንዲያዘጋጁ ወንድሞችን ማለድሁ፤ እንደዚህም የተዘጋጀ ይሁን፤ በረከትን እንደምታገኙበት እንጂ በንጥቂያ እንደ ተወሰደባችሁ አይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ እንደ በረከት ሆኖ ከስስት የማይሆን ይህ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን በረከት አስቀድመው እንዲፈጽሙ ወንድሞችን እለምን ዘንድ እንዲያስፈልገኝ አሰብሁ። |
ስለዚህ እባክህ ይህን ያቀረብኩልህን ስጦታ ተቀበለኝ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ሰጥቶኛል” አለ። ስጦታውን እንዲቀበለው ያዕቆብ ዔሳውን አጥብቆ ለመነው። እርሱም ተቀበለው።
ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።
በዚህ ነገር በእናንተ ላይ ያለን ትምክሕት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር እነዚህን ወንድሞች እልካለሁ፤ እናንተም ልክ እኔ ከዚህ በፊት እንዳልኩት ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ።
እርስዋም “የሰጠኸኝ መሬት በረሓማ ላይ ስለ ሆነ ጥቂት የውሃ ምንጮች እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ፤” አለችው፤ ስለዚህ ካሌብ የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።
ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በተመለሰ ጊዜ ከምርኮው ከፊሉን ወዳጆቹ ለሆኑት ለይሁዳ ሽማግሌዎች ላከላቸው፤ ከላከላቸውም ምርኮ ጋር “ይህ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ተወስዶ የተላከላችሁ ስጦታ ነው” የሚል መልእክት ነበር፤