Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 9:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ወደ እናንተ መጥተው ያልተዘጋጃችሁ ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ በእናንተ በመመካታችን እናፍራለን፤ እናንተማ በጣም ታፍራላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋራ መጥተው ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ፣ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ እኛም ያን ያህል በእናንተ በመመካታችን እናፍራለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡና ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ፥ ያን ያህል ማለታችን እንድታፍሩ ባይሆንም፥ እንዲህ በመመካታችን ግን እንድናፍር ያደርገናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ምና​ል​ባት የመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመ​ጡና ሳታ​ዘ​ጋጁ ቢያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ እና​ንተ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ ባል​ልም እኛ ስለ እና​ንተ ከነ​ገ​ር​ና​ቸው የተ​ነሣ እና​ፍ​ራ​ለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡ፥ ያልተዘጋጃችሁም ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ፥ እናንተ እንድታፍሩ አላልንም እኛ ግን በዚህ እምነታችን እንድናፍር አይሁን።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 9:4
7 Referencias Cruzadas  

ይኸውም የመቄዶንያና በአካይያ የሚገኙ የእግዚአብሔር ወገኖች በኢየሩሳሌም ላሉት ድኾች የገንዘብ ርዳታ ለመላክ በፈቃዳቸው ስለ ወሰኑ ነው።


እኔ በምመጣበት ጊዜ የገንዘብ መዋጮ እንዳይደረግ በየሳምንቱ እሑድ ከእናንተ እያንዳንዱ በሚያገኘው ገቢ መጠን እያዋጣ ለይቶ ያስቀምጥ።


እንደዚሁ በትምክሕት ስናገር የምናገረው እንደ ጌታ ፈቃድ ሳይሆን እንደ ሞኝ ሆኜ ነው።


ስለዚህ ፍቅራችሁን ግለጡላቸው፤ በዚህ ዐይነት ፍቅራችንና በእናንተ ላይ ያለን ትምክሕት ከንቱ አለመሆኑን ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ ታሳያላችሁ።


“የዐካይያ ሰዎች ከዐለፈው ዓመት ጀምረው ለመርዳት ዝግጁዎች ናቸው” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ ስለ እናንተ የምመካው ትጋታችሁን ስለማውቅ ነው፤ የእናንተም ትጋት ሌሎችን አነሣሥቶአል።


እነሆ እኔ ጳውሎስ “ዕዳውን እከፍልሃለሁ” ብዬ በገዛ እጄ ጽፌ አረጋግጥልሃለሁ፤ ሆኖም ስለ ሕይወትህ አንተ ራስህ እንኳ የእኔ ባለዕዳ መሆንክን እኔ ላስታውስህ አያስፈልግም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos