ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።
2 ቆሮንቶስ 6:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክርስቶስና ዲያብሎስ እንዴት ሊስማሙ ይችላሉ? የሚያምንና የማያምንስ በምን ሊወዳጁ ይችላሉ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክርስቶስ ከቤልሆር ጋራ ምን ስምምነት አለው? የሚያምን ከማያምን ጋራ ምን ኅብረት አለው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን ስምምነት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክርስቶስን ከቤልሆር ጋር አንድ የሚያደርገው ማን ነው? ወይስ ምእመናንን ከመናፍቃን ጋር አንድ ወገን የሚያደርጋቸው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? |
ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።
ነገር ግን ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የጐሣ መሪዎች ሁሉ እነዚህን ሰዎች፦ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ስለምንሠራው ቤተ መቅደስ የእናንተ ርዳታ አያስፈልገንም፤ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ቂሮስ ባዘዘን መሠረት እኛው ራሳችን እንሠራዋለን” ሲሉ መለሱላቸው።
እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።
እየተደሰቱ ሳለም ከከተማይቱ የመጡ ጋጠወጦች በድንገት ቤቱን ከበው በሩን መደብደብ ጀመሩ፤ ሽማግሌውንም “ያንን ወደ ቤትህ የገባውን ሰው ግብረ ሰዶም እንድንፈጽምበት አውጣልን!” አሉት።
እነርሱን ገድለን ይህን ክፉ ነገር ከእስራኤል እናስወግድ ዘንድ እነዚያን በጊብዓ ያሉትን ነውረኞች አሳልፋችሁ ስጡን።” የብንያም ሕዝብ ግን የቀሩት እስራኤላውያን የነገሩአቸውን ነገር አልተቀበሉም፤