Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ታዲያ፥ አንድ ክርስቲያን ሌላውን ክርስቲያን ከሶ ወደ አሕዛብ ፍርድ ቤት መውሰድ ይገባዋልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ለመክሰስ ፍርድ ቤት ይሄዳል፤ ያውም በማያምኑ ሰዎች ፊት!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ይከሳል፤ ይህም በማያምኑ ፊት ይደረጋል!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ነገር ግን ወን​ድም ከወ​ን​ድሙ ጋር ይካ​ሰ​ሳል፤ ይህም በማ​ያ​ምኑ ፊት ይደ​ረ​ጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ይከሳል፥ ይህም በማያምኑ ፊት ይደረጋልን?

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 6:6
13 Referencias Cruzadas  

በዚህ ሁኔታ ወንድሞቹን ካሰናበታቸው በኋላ “በመንገድ አትጣሉ” ብሎ መከራቸው።


በማግስቱም ሁለት እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኘና ሊገላግላቸው በመፈለግ ‘እናንተ ሰዎች፥ እናንተ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለምን ትጣላላችሁ?’ አላቸው።


ከእናንተ አንዱ ክርስቲያን ከሆነው ወንድሙ ጋር ቢጣላ ጉዳዩን ክርስቲያኖች በፍርድ እንዲያዩለት በማድረግ ፈንታ ለክስ ወደ አሕዛብ የፍርድ ሸንጎ ለመሄድ እንዴት ይደፍራል?


እንዲያውም እርስ በርሳችሁ ተካሳችሁ መሟገት ራሱ ለእናንተ ውርደት ነው፤ ይልቅስ እናንተ ብትበደሉ አይሻልምን? እንዲሁም እናንተ ብትታለሉ አይሻልምን?


በማይመች ሁኔታ ከማያምኑ ሰዎች ጋር አትጣመሩ፤ ጽድቅና ኃጢአት እንዴት ሊተባበሩ ይችላሉ? ብርሃንና ጨለማ እንዴት አብረው ሊኖሩ ይችላሉ?


ክርስቶስና ዲያብሎስ እንዴት ሊስማሙ ይችላሉ? የሚያምንና የማያምንስ በምን ሊወዳጁ ይችላሉ?


ለራሱ ዘመዶች፥ ይልቁንም ለቅርብ ቤተሰቦቹ የማያስብ ሃይማኖቱን የካደ ነው፤ እንዲያውም ከማያምን ሰው እንኳ የባሰ ክፉ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos