2 ቆሮንቶስ 12:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም እንኳ በመመካት ጥቅም ባይገኝበት መመካት ካስፈለገ ጌታ በሰጠኝ መገለጥና ራእይ እመካለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመመካት የሚገኝ ጥቅም ባይኖርም፣ መመካት ካስፈለገ ከጌታ ወደ ተቀበልሁት ራእይና መገለጥ አመራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመመካት የሚገኝ ጥቅም ባይኖርም፥ መመካት ካስፈለገ ከጌታ ወደ ተቀበልሁት ራእይና መገለጥ አመራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ መመካት ይቻለኛል፤ ነገር ግን አይጠቅምም፤ ደግሞም ወደ ጌታ ራእይና መገለጥ እሄዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትምክህት የሚያስፈልግ ነው፤ አይጠቅምም ነገር ግን ከጌታ ወዳለው ራእይና መገለጥ እመጣለሁ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤
እኔ ግን እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፤ እኔ ካልሄድኩ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ከሄድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በተለያዩ ቋንቋዎች እየተናገርኩ ብመጣ ምን እጠቅማችኋለሁ? ይልቅስ የምጠቅማችሁ የእግዚአብሔርን ምሥጢር መግለጥን፥ ዕውቀትን፥ ትንቢት መናገርን፥ ትምህርትን ይዤላችሁ ብመጣ ነው።
“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ግን ሁሉም ነገር ይጠቅመኛል ማለት አይደለም፤ ሁሉም ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ይሁን እንጂ ለማናቸውም ነገር ባሪያ ሆኜ አልገዛም፤
እንደ ሞኝ ተናገርኩ! ታዲያ፥ እንዲህ እንድናገር ያደረጋችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ እኔን ማመስገን የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ፤ እኔ ማንነቴ ያልታወቀ ሰው ብሆንም እንኳ ታላላቅ ከተባሉት ሐዋርያት በምንም አላንስም።
ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል።
ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ።
በዚህ ጉዳይ ለእናንተ መልካም መስሎ የታየኝን ምክር እሰጣችኋለሁ፤ ባለፈው ዓመት ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ይህን ለማድረግ በመጀመሪያ የፈለጋችሁት እናንተ ነበራችሁ።
የሄድኩትም እግዚአብሔር በገለጠልኝ መሠረት ነው። ከዚህ በፊት የሠራሁትም ሆነ አሁን የምሠራው ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር በማለት ለአሕዛብ የምሰብከውን ወንጌል ታላላቅ ለሆኑት መሪዎች በግል አስታወቅኋቸው።
የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።