እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው አራዊት ሁሉ፥ እባብ እጅግ ተንኰለኛ ነበረ፤ ስለዚህ እባብ “በአትክልቱ ቦታ ካሉት ዛፎች ሁሉ ፍሬ እንዳትበሉ በእርግጥ እግዚአብሔር አዞአችኋልን?” ሲል ሴቲቱን ጠየቃት።
2 ቆሮንቶስ 11:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት ምናልባት የእናንተም ሐሳብ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ያላችሁን ቅንና ንጹሕ የሆነ ታማኝነት ትተዋላችሁ ብዬ እፈራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰል እንዳሳታት ምናልባት የእናንተም ልቡና ተበላሽቶ ለክርስቶስ ካላችሁ ቅንነትና ንጽሕና እንዳትወሰዱ እሠጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ሊኖራችሁ ከሚገባ ቅንነትና ንጽሕና እንዳትርቁ ብዬ እፈራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ከክርስቶስ የዋህነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። |
እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው አራዊት ሁሉ፥ እባብ እጅግ ተንኰለኛ ነበረ፤ ስለዚህ እባብ “በአትክልቱ ቦታ ካሉት ዛፎች ሁሉ ፍሬ እንዳትበሉ በእርግጥ እግዚአብሔር አዞአችኋልን?” ሲል ሴቲቱን ጠየቃት።
ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ እነርሱ ቢቻላቸውስ የእግዚአብሔርን ምርጦች እንኳ ለማሳሳት ታላላቅ ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።
እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።
ስጦታችን መምከር ከሆነ እንምከር፤ ስጦታችን መለገሥ ከሆነ ከልብ እንለግሥ፤ ስጦታችን ማስተዳደር ከሆነ በትጋት እናስተዳድር፤ ስጦታችን ርኅራኄ ማድረግ ከሆነ ይህንኑ በደስታ እናድርግ።
የምንመካበት ነገር ይህ ነው፤ ይህም እውነት መሆኑን ኅሊናችን ይመሰክርልናል፤ ከሌሎች ሰዎችና በተለይም ከእናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት ከእግዚአብሔር ባገኘነው ቅድስናና ቅንነት የተመሠረተ ነው፤ ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ጸጋ ነበር እንጂ በሰው ጥበብ አልነበረም።
እንዲሁም ማንም እንደ ባሪያ ቢያደርጋችሁ፥ ማንም ቢበዘብዛችሁ፥ ማንም ቢጠቀምባችሁ፥ ማንም ቢንቃችሁ፥ ማንም ፊታችሁን በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሣላችሁ።
እኛ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ንግድ ዕቃ እንደሚቸረችሩት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላኩ ቅን መልእክተኞች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንናገራለን።
ስውርና አሳፋሪ የሆነውን ነገር አስወግደናል፤ በተንኰልም አንሠራም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አንለውጥም፤ ይልቅስ እውነትን በይፋ እናሳያለን፤ ራሳችንንም ለሰው ሁሉ ኅሊና በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ እናደርጋለን።
ነገር ግን በመካከላችን ሾልከው በስውር የገቡ አንዳንድ ሐሰተኞች ወንድሞች እንዲገረዝ ፈልገው ነበር፤ እነዚህ ሰዎች ለስለላ በመካከላችን ሠርገው የገቡት በኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን ነጻነት ነጥቀው ወደ ባሪያነት ሊመልሱን አስበው ነው።
እናንተ ሞኞች የገላትያ ሰዎች! ማን አፍዝ አደንግዝ አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ተሰቅሎ በፊት ለፊታችሁ በግልጥ ይታይ ነበር።
ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች የተንኰል ሽንገላና አታላይነት በተዘጋጀ በአሳሳች የትምህርት ነፋስና ሞገድ ወዲያና ወዲህ ተገፍትረው እንደሚወሰዱ ሕፃናት አንሆንም።
በአጉል ትሕትናና መላእክትን በማምለክ የሚመካ ማንም ሰው ያለ ዋጋ እንዳያስቀራችሁ ተጠንቀቁ፤ እንዲህ ዐይነቱ ሰው ስለሚያየው ራእይ እየተመጻደቀ ከንቱና ሥጋዊ በሆነ አስተሳሰብ ይታበያል።
በክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በሰው ሠራሽ ወግና በዓለማዊ ተራ ሥርዓት ላይ በተመሠረተ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳያጠምዳችሁ ተጠንቀቁ።
በዚህ ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ በትዕግሥት መጠበቅ ባለመቻሌ ስለ እምነታችሁ ማወቅ ፈልጌ ጢሞቴዎስን ወደ እናንተ ላክሁት፤ እርሱን የላክሁትም ምናልባት ፈታኙ በአንድ መንገድ ፈትኖአችሁ ይሆናል፤ ሥራችንም ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል በማለት ፈርቼ ነው።
ወደ መቄዶንያ ስሄድ ሳለሁ ዐደራ እንዳልኩህ እዚያ ያሉ አንዳንድ ሰዎች የሐሰት ትምህርት እንዳያስተምሩ ታደርጋቸው ዘንድ በኤፌሶን ተቀመጥ።
ባልተለመደ በልዩ ልዩ ዐይነት ትምህርት አትማረኩ፤ ልባችን የመብል ሥነ ሥርዓቶችን በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋ ቢጸና መልካም ነው፤ ይህን የምግብ ሥነ ሥርዓት የተከተሉ ሰዎች ምንም አልተጠቀሙም።
ልጆቼ ሆይ! ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ “የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል” ሲባል ሰምታችኋል፤ እነሆ፥ አሁን እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ በዚህ ምክንያት የመጨረሻው ሰዓት መሆኑን እናውቃለን።
ወዳጆች ሆይ! በዓለም ላይ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ስለ ተነሡ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ይልቅስ መንፈሶች የእግዚአብሔር መሆናቸውንና አለመሆናቸውን መርምሩ።
የሚፈረድባቸው መሆኑ ከብዙ ጊዜ በፊት የተጻፈባቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እናንተ ሾልከው ገብተዋል፤ እነርሱ የአምላካችንን ጸጋ በስድነት የሚለውጡ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ናቸው፤ እርሱ ብቻ ገዢአችንና ጌታችን የሆነን ኢየሱስ ክርስቶስንም ይክዳሉ።
ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።