2 ቆሮንቶስ 10:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦር መሣሪያዎቻችንም ምሽግ ለማፍረስ የሚያስችል መለኮታዊ ኀይል ያላቸው ናቸው እንጂ ዓለማዊ የጦር መሣሪያዎች አይደሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም የምንዋጋበት የጦር መሣሪያ የዚህ ዓለም መሣሪያ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደምሰስ የሚችል መለኮታዊ ኀይል ያለው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለም፤ ምሽግን ለመስበር መለኮታዊ ኃይል አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ጽኑ ምሽግን በሚያፈርስ በእግዚአብሔር ኀይል ነው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ |
እንዲሁም የሰውነታችሁን ክፍሎች የዐመፅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታስገዙ፤ ነገር ግን ከሞት ተነሥታችሁ ሕያዋን እንደ ሆናችሁ በማድረግ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የሰውነታችሁንም ክፍሎች ሁሉ የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አስገዙ።
ያለ ደመወዝ በራሱ ገንዘብ በወታደርነት የሚያገለግል ማነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላስ ማነው? መንጋ እየጠበቀ የመንጋውን ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
ይህን መልእክት ከእናንተ ርቄ ሳለሁ የጻፍኩላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ጌታም በሰጠኝ ሥልጣን አላስጨንቃችሁም፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ አይደለም።
ነገር ግን ይህ ከሁሉ የሚበልጠው ኀይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ አለመሆኑ እንዲታወቅ ይህን ክቡር ነገር እንደ ሸክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል።
እኛ ግን የብርሃን ሰዎች ስለ ሆንን ራስን በመግዛት በመጠን እንኑር፤ እምነትንና ፍቅርን እንደ ጥሩር እንልበስ፤ የመዳንን ተስፋ እንደ ራስ ቊር እንልበስ፤
ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! ከዚህ ቀደም ስለ አንተ በትንቢት በተነገረው መሠረት የሚከተለውን ትእዛዝ በዐደራ እሰጥሃለሁ፤ ትንቢቱን በመከተል መልካም ጦርነትን ተዋጋ፤
ስለዚህ እምቢልታ ተነፋ፤ ሕዝቡም የእምቢልታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ ከፍተኛ የጩኸት ድምፅ አሰሙ የከተማይቱም ቅጽሮች ፈረሱ፤ ከዚህም በኋላ ሠራዊቱ ኮረብታውን ወጥቶ ሰተት ብሎ ወደ ከተማይቱ በመግባት በቊጥጥሩ ሥር አደረጋት፤