2 ቆሮንቶስ 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ! በእስያ ክፍለ ሀገር በነበርንበት ጊዜ የደረሰብንን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ ይህም የደረሰብን መከራ ልንሸከመው ከምንችለው በላይ ወድቆብን ስለ ነበር በሕይወት ለመኖር የነበረን ተስፋ እንኳ ተቋርጦ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ በእስያ ስለ ደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወድዳለን፤ በሕይወት ለመኖር እንኳ ተስፋ እስከምንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ የሆነ ጽኑ መከራ ደርሶብን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን ብታውቁት እንወዳለን፤ በሕይወታችን ተስፋ እስክመቁረጥ የሚያደርስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን ሆይ፥ በእስያ መከራ እንደ ተቀበልን ልታውቁ እወዳለሁ፤ ለሕይወታችን ተስፋ እስክንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ እጅግ መከራ ጸንቶብን ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤ |
ወንድሞቼ ሆይ! በሌሎች አሕዛብ መካከል ብዙ አማኞችን እንዳገኘሁ እንዲሁም በእናንተ መካከል አማኞችን ለማግኘት ፈልጌ ነበር፤ ነገር ግን ወደ እናንተ ለመምጣት ብዙ ጊዜ ዐቅጄ እስከ አሁን ያልተሳካልኝ መሆኑን እንድታውቁ እወዳለሁ።
እንደ ሰው አስተሳሰብ እኔ በኤፌሶን ከአራዊት ጋር መታገሌ ጥቅሜ ምንድን ነው? ሙታን ከሞት የማይነሡ ከሆነማ “ነገ ስለምንሞት ኑ እንብላ፤ እንጠጣ” እንደ ተባለው መሆኑ ነው።
አሁንማ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሁሉ አግኝታችኋል፤ አሁንማ ሀብታሞች ሆናችኋል፤ ከእኛም ተለይታችሁ ነግሣችኋል፤ በእርግጥ ብትነግሡማ ኖሮ፥ እኛም ከእናንተ ጋር አብረን ስለምንነግሥ መንገሣችሁ መልካም በሆነ ነበር፤
እንዲያውም ሞት እንደ ተፈረደብን ያኽል ተሰምቶን ነበር፤ ይህም ሁሉ የደረሰብን፥ የምንተማመነው ሙታንን በሚያስነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን ኀይል አለመሆኑን እንድንገነዘብ ነው።
ዳዊት ግን “አባትህ አንተ እኔን ምን ያኽል እንደምትወደኝ በደንብ ያውቃል፤ ስለዚህም ዕቅዱን አንተ እንድታውቅበት ላለማድረግ ወስኖአል፤ ይህንንም የሚያደርገው አንተ ይህን ብታውቅ በብርቱ እንደምታዝን ስለሚያውቅ ነው፤ በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከአሁን ወዲያ ወደ ሞት ለመድረስ የቀረችን አንዲት ዕርምጃ ብቻ ናት!” አለው።
ዳዊት በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፤ “አንድ ቀን ሳኦል እኔን ይገድለኛል፤ እንግዲህ ለእኔ የሚበጀኝ ነገር አምልጬ ወደ ፍልስጥኤም መሄድ ነው፤ ከዚያም በኋላ ሳኦል በእስራኤል ምድር እኔን መፈለጉን ስለሚተው ከእጁ አመልጣለሁ።”