2 ዜና መዋዕል 8:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሰሎሞን በላይኛውና በታችኛው ቤትሖሮን በብረት መዝጊያ ሊዘጉ የሚችሉ ቅጽር በሮች ያሉአቸው የተመሸጉ ከተሞችን እንደገና ሠራ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የላይኛውን ቤትሖሮንና የታችኛውን ቤትሖሮን የተመሸጉ ከተሞች አድርጎ ከቅጥሮቻቸው፣ ከበሮቻቸውና ከመዝጊያዎቻቸው ጋራ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ መቀርቀሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤት-ሖሮን ታችኛውንም ቤት-ሖሮን ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ፥ መወርወሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤትሖርን፥ ታችኛውንም ቤትሖርን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ መወርወሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤትሖሮን ታችኛውንም ቤትሖሮን ሠራ። |
ኤፍሬም፥ ሼኢራ ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ወለደ፤ እርስዋም የላይኛውንና የታችኛውን ቤትሖሮን፥ እንዲሁም ዑዜንሼኢራ ተብለው የሚጠሩትን ከተማዎች አሠራች።
አሳ የይሁዳን ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ግንቦችን፥ ቅጽሮችንና በብረት መወርወሪያ የሚዘጉ የቅጽር በሮችን በመሥራት፥ ከተሞቻችንን እንመሽግ፤ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለ ፈጸምን፥ እነሆ፥ ምድሪቱ በቊጥጥራችን ሥር ናት፤ እግዚአብሔር ጠብቆናል፤ በሁሉም አቅጣጫ የሰላም ዋስትና ሰጥቶናል፤” ሕዝቡም ከተሞችን መሸገ፤ በለጸገም፤
የባዕላት ከተማ፥ ስንቅና ትጥቅ የሚያስቀምጥባቸው ከተሞች ሁሉ፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚኖሩባቸው ከተሞች፤ በዚህም ዐይነት ሰሎሞን በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በእርሱ አስተዳደር ባለው ግዛት በሙሉ ሊሠራ ያቀዳቸውን የግንባታ ሥራዎች ሁሉ ፈጸመ።
ከዚያም በምዕራብ በኩል ወደሚገኙት ወደ ያፍሌጣውያን ይዞታ በመዝለቅ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ይደርሳል፤ ከዚያም ወደ ጌዜር ያልፍና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል።