Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 8:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የባዕላት ከተማ፥ ስንቅና ትጥቅ የሚያስቀምጥባቸው ከተሞች ሁሉ፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚኖሩባቸው ከተሞች፤ በዚህም ዐይነት ሰሎሞን በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በእርሱ አስተዳደር ባለው ግዛት በሙሉ ሊሠራ ያቀዳቸውን የግንባታ ሥራዎች ሁሉ ፈጸመ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ደግሞም ባዕላትንና የሰሎሞን ዕቃ ማከማቻ ከተሞች፣ እንዲሁም ሠረገለኞችና ፈረሰኞች የሚቀመጡባቸውን ከተሞች ሁሉ፣ በአጠቃላይ በኢየሩሳሌም፣ በሊባኖስና በግዛቶቹ ሁሉ ለመሥራት የፈለጋቸውን ነገሮች ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ባዓላትንም፥ ለሰሎሞንም የነበሩትን ለግምጃ ቤት የሚያገለግሉ ከተሞች ሁሉ፥ የሠረገላውንም ከተሞች ሁሉ፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም በሊባኖስም በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ለመሥራት የፈለገውን ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ባዕ​ላ​ት​ንም፥ ለሰ​ሎ​ሞ​ንም የነ​በ​ሩ​ትን የዕቃ ቤት ከተ​ሞች ሁሉ፥ የሰ​ረ​ገ​ላ​ው​ንም ከተ​ሞች ሁሉ፥ የፈ​ረ​ሰ​ኞ​ች​ንም ከተ​ሞች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በሊ​ባ​ኖ​ስም፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ምድር ሁሉ ሰሎ​ሞን ይሠራ ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ባዓላትንም፥ ለሰሎሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፥ የሠረገላውንም ከተሞች ሁሉ፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም በሊባኖስም በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ይሠራ ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 8:6
13 Referencias Cruzadas  

ሰሎሞንም ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሉ ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም፥ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ፤


“የሊባኖስ ደን” ተብሎ የተጠራው አዳራሽ ርዝመቱ አርባ አራት ሜትር፥ ወርዱ ኻያ ሁለት ሜትር፥ ቁመቱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር፤ አዳራሹም በእያንዳንዱ ረድፍ ዐሥራ አምስት ሆነው በሦስት ረድፍ የቆሙ አርባ አምስት ምሰሶዎች ነበሩት፤ በምሰሶዎቹም ላይ የተጋደሙ፥ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠሩ ሠረገሎችና በየመካከላቸው የገቡ ሳንቃዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም በላይ በምሰሶዎቹ የተደገፉ ዕቃ ቤቶች ነበሩ፤ የእነዚህም ዕቃ ቤቶች ጣራ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር፤


ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱንና ሊሠራው የፈለገውን ሌላውንም ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፥


ሰሎሞን በአንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና በዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች የተጠናከረ ሠራዊትን አደራጀ፤ ከእነርሱም ከፊሉን በኢየሩሳሌም፥ የቀረውን ደግሞ በሌሎች ልዩ ልዩ ከተሞች በመመደብ በዚያው እንዲኖሩ አደረገ።


ስለዚህ ኢዮሣፍጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ገናና እየሆነ ሄደ፤ በመላው ይሁዳ ምሽጎችንና፥ እጅግ የበዛ ስንቅና ትጥቅ የተከማቹባቸውን ከተማዎች ሠራ። በኢየሩሳሌምም የተለየ ችሎታ ያላቸውን ተዋጊዎች አኖረ፤


በበረሓ የምትገኘውን የታጽሞርን ከተማና በሐማት ያለውን የስንቅና የትጥቅ ማኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ አጠናከረ፤


እንዲሁም ሰሎሞን በላይኛውና በታችኛው ቤትሖሮን በብረት መዝጊያ ሊዘጉ የሚችሉ ቅጽር በሮች ያሉአቸው የተመሸጉ ከተሞችን እንደገና ሠራ፤


ሰሎሞን በጒልበት ሥራ ያሰማራቸው ገባሮች፥ እስራኤላውያን ምድራቸውን ርስት አድርገው በያዙ ጊዜ ያልገደሉአቸው የከነዓን ሕዝብ ዘሮች ነበሩ፤ እነዚህም የከነዓን ዘሮች እስከ አሁን ድረስ ባሪያዎች ሆነው የሚያገለግሉ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ናቸው፤


ደግሞም አንድ ትልቅ ነገር ፈጸምኩ፤ ይኸውም፥ መኖሪያ ቤቶችን ሠራሁ፤ ወይን ተከልኩ፤


ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ወደ እኔ ነይ፤ ከሊባኖስ ወደ እኔ ነይ፤ ከአማና ተራራ ጫፍ ውረጂ፤ የአንበሳና የነብር መኖሪያ ከሆኑት ከሠኒርና ከሔርሞን ተራራዎች ወርደሽ ነይ


ኤልተቄን፥ ጊበቶንን፥ ባዕላትን፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos