2 ዜና መዋዕል 2:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ኪራምም ለንጉሥ ሰሎሞን በደብዳቤ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚወድ አንተ በእነርሱ ላይ እንድትነግሥ አደረገ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጢሮስ ንጉሥ ኪራምም ለሰሎሞን እንዲህ ሲል በደብዳቤ መለሰለት፤ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚወድድ አንተን በእነርሱ ላይ አነገሠህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጢሮስ ንጉሥም ኪራም ለሰሎሞን በላከው ደብዳቤ እንዲህ ብሎ መለስ ሰጠ፦ “ጌታ ሕዝቡን ወድዶአልና በእነርሱ ላይ አነገሠህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጢሮስ ንጉሥ ኪራምም፥ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ወድዶአልና በላያቸው አነገሠህ” ሲል ለሰሎሞን ጻፈለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጢሮስ ንጉሥ ኪራምም “እግዚአብሔር ሕዝቡን ወድዶአልና በላያቸው አነገሠህ፤” ብሎ ለሰሎሞን መልእክት ላከ። |
አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን! እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል።”
ንጉሥ ሆነህ በእርሱ ስም ትገዛ ዘንድ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ ለማድረግ መልካም ፈቃዱ ስለ ሆነ አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን! በፍቅሩም እስራኤል ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር ስለ ፈለገ ሕግና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ አንተን መርጦ ንጉሥ አድርጎሃል።”
የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።