Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ንጉሥ ሆነህ በእርሱ ስም ትገዛ ዘንድ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ ለማድረግ መልካም ፈቃዱ ስለ ሆነ አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን! በፍቅሩም እስራኤል ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር ስለ ፈለገ ሕግና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ አንተን መርጦ ንጉሥ አድርጎሃል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በአንተ ደስ ተሰኝቶ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ንጉሥ ሆነህ እንድትገዛ፣ በዙፋኑ ላይ ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን፤ አምላክህ ለእስራኤል ካለው ፍቅርና ለዘላለም ሊያጸናቸው ካለው ፍላጎት የተነሣ፣ ፍትሕና ጽድቅ እንዲሰፍን ታደርግ ዘንድ አንተን በላያቸው ላይ አንግሦሃል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በአምላክህ በጌታ ፊት ንጉሥ እንድትሆን በዙፋኑ ላይ ሊያስቀምጥህ የወደደህ አምላክህ ጌታ ብሩክ ይሁን፤ አምላክህ እስራኤልን ለዘለዓለም ሊያጸናቸው ወድዶአቸዋልና ስለዚህ ፍርድና ጽድቅ እንድታደርግ በእነርሱ ላይ አነገሠህ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን በዙ​ፋኑ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጥህ ዘንድ የወ​ደ​ደህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ይሁን፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ና​ቸው ዘንድ ወድ​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ታደ​ርግ ዘንድ በላ​ያ​ቸው አነ​ገ​ሠህ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ንጉሥ እንድትሆን በዙፋኑ ላይ ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደህ አምላክህ እግዚአብሔር ብሩክ ይሁን፤ አምላክህ እስራኤልን ለዘላለም ያጸናቸው ዘንድ ወድዶአቸዋልና ስለዚህ ፍርድና ጽድቅ ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:8
31 Referencias Cruzadas  

የእስራኤል አምላክ ይህን ተናግሮአል፤ የእስራኤል ጠባቂ እንዲህ ብሎኛል፤ “እግዚአብሔርን በመፍራትና በፍትሕ የሚያስተዳድር ንጉሥ፥


በዚህ ዐይነት ዳዊት የመላው እስራኤል ንጉሥ ሆኖ ሕዝቡ ዘወትር ትክክለኛ ፍርድ ማግኘት እንዲችል ጥረት ያደርግ ነበር፤


አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን! እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል።”


እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።


እስራኤልን ዘለዓለም የራስህ ሕዝብ አደረግህ፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተም አምላካቸው ሆንክ።


ለእኔም ብዙ ወንዶች ልጆችን ሰጠኝ፤ ነገር ግን የሚቀጥለው የእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ የመረጠው ልጄን ሰሎሞንን ነው።”


እዚያም በመላው ጉባኤ ፊት ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፦ “የቀድሞ አባታችን የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገንክ ሁን!


ከዚህ በኋላ ዳዊት ሕዝቡን “አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ!” አለ፤ መላው ጉባኤም የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ወደ መሬት ለጥ ብለውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ለንጉሡም ክብር ሰጡ።


በዚህ ዐይነት ሰሎሞን በአባቱ እግር ተተክቶ እግዚአብሔር ባጸናው ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ እርሱም ሁሉ ነገር የተሳካለት ንጉሥ ሆነ፤ መላውም የእስራኤል ሕዝብ ታዘዙለት፤


አሁንም እናንተ እግዚአብሔር ለዳዊት ዘሮች የሰጠውን የመንግሥት ሥልጣን በመድፈር ለመቃወም ዐቅዳችኋል፤ ይህ ዕቅዳችሁ ግቡን እንዲመታ ለማድረግም እጅግ ብዙ የሆነ የጦር ሠራዊት አሰልፋችኋል፤ ለእናንተ አማልክት እንዲሆኑ ኢዮርብዓም ከወርቅ ያሠራቸውን የጥጃ ምስሎች ይዛችሁ መጥታችኋል።


እንጨት ለሚቈርጡ ለሠራተኞችህ ስንቅ የሚሆን ሁለት ሚሊዮን ኪሎ ስንዴ፥ ሁለት ሚሊዮን ኪሎ ገብስ፥ አራት መቶ ሺህ ሊትር የወይን ጠጅና አራት መቶ ሺህ ሊትር የወይራ ዘይት እልክልሃለሁ።”


ንጉሥ ኪራምም ለንጉሥ ሰሎሞን በደብዳቤ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚወድ አንተ በእነርሱ ላይ እንድትነግሥ አደረገ።”


ዘወትር በአንተ ፊት በመገኘት ጥበብ የተሞላበት ንግግርህን የሚሰሙ ባለሟሎችና አገልጋዮችህ እንዴት የታደሉ ናቸው!


ንግሥተ ሳባ ያመጣችውን ከአራት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፥ እጅግ ብዙ ሽቶና ዕንቊ ገጸ በረከት አድርጋ ለሰሎሞን ሰጠችው፤ እርስዋ ለሰሎሞን የሰጠችው የሽቶ ዐይነት፥ ከዚያ በፊት ከቶ ታይቶ የማይታወቅ ነው።


ወደ ሰፊ ቦታ አወጣኝ፤ በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ።


“እግዚአብሔር ያድነው ዘንድ በእርሱ ተማምኖአልና የሚወደው ከሆነ እስቲ ያድነው” ይላሉ።


በዚህ ዐይነት ሕዝብህን በትትክል ያስተዳድራል፤ ለጭቊኖችህም በትክክል ይፈርዳል።


ፍትሕን የምትወድ ኀያል ንጉሥ ሆይ! ቅንነትን መሥርተሃል፤ በእስራኤል ዘንድ ፍትሕንና ጽድቅን ተግባራዊ አድርገሃል።


መሥዋዕት ከማቅረብ እውነተኛ ይልቅ ትክክልና የሆነውን ነገር ማድረግ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።


ንጉሥ ፍትሕ እንዳይጓደል በሚያደርግበት ጊዜ ሀገሩን ያረጋጋል፤ ሕዝብን የሚበዘብዝ መሪ ግን ሀገሩን ወደ ጥፋት ያደርሳል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።


ከእንግዲህ ወዲህ “የተተወች” ተብለሽ አትጠሪም፤ ምድርሽም “ባድማ” ተብላ አትጠራም። የምትጠሪበትም አዲስ ስም፥ “እግዚአብሔር በእርስዋ ደስ ይለዋል!” የሚል ይሆናል፤ ምድርሽም “ባለ ባል” ተብላ ትጠራለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ ምድርሽም ባል እንዳላት ሴት ትሆናለች።


ለንጉሣዊ ሥልጣኑ ወሰን የለውም፤ መንግሥቱም ዘለዓለማዊ ሰላም የሰፈነበት ይሆናል፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፥ እውነትና ፍትሕ የሰፈነበት መንግሥት በዳዊት ዙፋን ላይ ተመሥርቶ እንዲጸና ያደርገዋል፤ የሠራዊት አምላክ ቅናት ይህን ለማድረግ ወስኖአል።


ነገር ግን እግዚአብሔር እናንተን ስለ ወደደ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የሰጠውን የተስፋ ቃል መጠበቅ ፈለገ፤ በታላቅ ኀይሉ ያዳናችሁና የግብጽ ንጉሥ ባርያዎች ከመሆን ነጻ ያወጣችሁም በዚህ ምክንያት ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos