ሰሎሞን በኖረበት ዘመን ሁሉ ሃዳድ ካደረሰበት ችግር በተጨማሪ ረዞን የእስራኤል ጠላት ሆነ። ስለዚህ ረዞን በሶርያ ላይ ገዢ ሆኖ በእስራኤል ላይ ጠላትነቱን ቀጠለ።
2 ዜና መዋዕል 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐዛርያስም ከንጉሥ አሳ ጋር ለመገናኘት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ አሳ ሆይ! አድምጠኝ! እናንተም የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ስሙኝ! እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ ሆናችሁ ድረስ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ከፈለጋችሁትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋራ ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋራ ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን፣ ይተዋችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳንም ሊያገኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ እናንተ ከጌታ ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተውት ግን ይተዋችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ንጉሡን አሳን፥ የይሁዳንና የብንያምን ሕዝብ ሁሉ ሊገናኝ ወጣ፤ እንዲህም አለ፥ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ብትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳንም ሊያገኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተውት ግን ይተዋችኋል። |
ሰሎሞን በኖረበት ዘመን ሁሉ ሃዳድ ካደረሰበት ችግር በተጨማሪ ረዞን የእስራኤል ጠላት ሆነ። ስለዚህ ረዞን በሶርያ ላይ ገዢ ሆኖ በእስራኤል ላይ ጠላትነቱን ቀጠለ።
ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
ከዚህ በኋላ ነቢዩ ሸማዕያ ሺሻቅን በመፍራት፥ በኢየሩሳሌም በአንድነት ተሰብስበው ወደ ነበሩ ወደ ንጉሥ ሮብዓምና ወደ ይሁዳ መሪዎች ሄዶ፥ “እግዚአብሔር ‘እኔን ስለ ተዋችሁ እነሆ፥ እኔም በሺሻቅ እጅ እንድትወድቁ ትቼአችኋለሁ’ ይላችኋል” አላቸው።
የእኛ መሪ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ የእግዚአብሔር ካህናትም መለከት ለመንፋት ተዘጋጅተው እዚህ ከእኛ ጋር ይገኛሉ፤ እነርሱ እምቢልታ መንፋት እንደ ጀመሩም እኛ በእናንተ ላይ ጦርነት እንከፍታለን፤ ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከቶ ድል ማድረግ ስለማትችሉ፥ ከቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት አትግጠሙ!”
ከዚህ በኋላ አቢያ ኰረብታማ በሆነ በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ጸማራይም ተራራ ወጥቶ ቆመ፤ ድምፁን ከፍ በማድረግም ለኢዮርብዓምና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ አድምጡኝ!
የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በፍጹም ልባቸው ይህን ቃል ኪዳን ስለ ገቡ ደስ ተሰኝተው ነበር፤ እግዚአብሔርንም አጥብቀው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር በመሆን በዙሪያቸው ሁሉ ሰላም እንዲኖር አደረገላቸው።
ያሐዚኤልም እንዲህ አለ፦ “ንጉሥ ሆይ! እናንተም የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በሙሉ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ተስፋ አትቊረጡ፤ ይህንንም ታላቅ ሠራዊት ለመቋቋም አትፍሩ፤ ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለም፤
በዚህ ጦርነት ላይ የምትዋጉ እናንተ አይደላችሁም፤ ስፍራ ስፍራችሁን ይዛችሁ ብቻ ጠብቁ፤ እግዚአብሔር ድልን እንደሚያጐናጽፋችሁ ታያላችሁ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! ሳታመነቱና በፍርሃት ሳትሸበሩ ነገ በቀጥታ ሄዳችሁ ተዋጉ! እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል!’ ”
ሰዎቹ በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሥተው ተቆዓ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓማ አገር ሄዱ፤ ወደዚያ ለመሄድ ጒዞ በመጀመር ላይ ሳሉም ኢዮሣፍጥ እነርሱን “የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ተማመኑ፤ እርሱም ብርታትን ይሰጣችኋል፤ የእግዚአብሔር ነቢያት የሚነግሩአችሁንም እመኑ፤ ይሳካላችኋልም” አላቸው።
ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ ወረደ፤ እርሱም ሕዝቡ ሊያዩት በሚችሉበት ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ቆሞ “እግዚአብሔር ‘ትእዛዞቼን ስለምን ትተላለፋላችሁ? በገዛ ራሳችሁስ ላይ ስለምን ጥፋትን ታመጣላችሁ?’ ሲል ይጠይቃችኋል፤ እንግዲህ እናንተ ስለ ተዋችሁት እርሱም ትቶአችኋል” አላቸው።
መንፈሳዊ አማካሪው ዘካርያስ በሕይወት እስከ ነበረበት ዘመን ድረስ ዖዝያ እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለግል ነበር፤ እግዚአብሔርም ባረከው።
ከእርሱ ጋር ያለው ኀይል ሰብአዊ ኀይል ነው፤ ከእኛ ጋር ሆኖ የሚረዳንና የሚዋጋልን ግን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፤” ሕዝቡም ንጉሡ በተናገረው በዚህ ቃል ተበረታታ።
ስለዚህም የአሦር ሠራዊት ይሁዳን እንዲወር እግዚአብሔር ፈቀደ፤ ሠራዊቱም ምናሴን ማርኮ በአፍንጫው ሥናጋ በማግባት በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
ኢዮስያስ በነገሠ በስምንተኛ ዓመቱ፥ ገና ወጣት ሳለ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን አምላክ እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመረ፤ ከአራት ዓመት በኋላም የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን፥ አሼራ ተብላ የምትጠራ የሴት አምላክ ምስሎችንና ሌሎችን ጣዖቶች ሁሉ ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ማስወገድ ጀመረ፤
ከዚህ በፊት ለንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ ባስረዳሁት ጊዜ “አምላካችን እግዚአብሔር በእርሱ የሚታመኑትን ሁሉ ይባርካል፤ እርሱን የሚተዉትን ግን በብርቱ ይቀጣቸዋል” በማለት ገልጬለት ስለ ነበረ በመንገድ ከሚገጥሙን ጠላቶቻችን እንዲጠብቁን ወታደሮችንና ፈረሰኞችን ይሰጠን ዘንድ ንጉሡን ጠይቄው ቢሆን ኖሮ ባፈርኩ ነበር።
ጨለማ በሆነ አገር በድብቅ አልተናገርኩም፤ የያዕቆብን ልጆች፦ ‘ቅርጽ በሌለው ቦታ ፈልጉኝ’ አላልኳቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር እውነቱን እናገራለሁ፤ ትክክል የሆነውንም ነገር እገልጣለሁ።
ለዚህም ኢሳይያስ ሲመልስ እንዲህ አለ “እናንተ የንጉሥ ዳዊት ቤተሰብ ሆይ! ስሙ፤ ሰውን ማሰልቸታችሁ አንሶ እግዚአብሔርንስ ማሳዘን ትፈልጋላችሁን?
በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉ ነገር አታድርጉ፤ ይህን ብታደርጉ ልክ እናንተ እንደምትሉት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።
ዐማሌቃውያንንና ከነዓናውያንን ፊት ለፊት ባያችሁ ጊዜ በጦርነት ትሞታላችሁ፤ እርሱን መከተል እምቢ ስላላችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም።”
“ጠላቶችህን ለመውጋት ስትዘምት፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን፥ ከአንተ የሚበልጥም ሠራዊት ባየህ ጊዜ ከግብጽ ምድር ያወጣህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ አትፍራቸው፤
ይህም በሚሆንበት ጊዜ እኔ በእነርሱ ላይ ተቈጥቼ እለያቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይደመሰሳሉ፤ በእነርሱም ላይ ብዙ አሠቃቂ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ፥ ‘ይህ ችግር የመጣብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደለምን?’ ይላሉ።
ያንን የሚናገረውን አንቀበልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ እግዚአብሔር በሰው አማካይነት ከምድር ሲናገራቸው አንሰማም ያሉት ካላመለጡ፥ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረንን ባንቀበል እንዴት እናመልጣለን!
ስለዚህም የአልዓዛር ልጅ ካህኑ ፊንሐስ እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን ዐወቅን፤ እናንተ በእርሱ ላይ አላመፃችሁም፤ ስለዚህም የእስራኤልን ሕዝብ ከእግዚአብሔር ቅጣት አድናችኋል።”
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ አዲስ ስም የተጻፈበትን ነጭ ድንጋይም እሰጠዋለሁ፤ ከተቀባዩ በቀር ይህን ሌላ ማንም አያውቀውም።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ‘ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካለው ከሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዲበላ አደርገዋለሁ።’
ኢዮአታም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ወደ ገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ እንዲህ በማለት ወደ እነርሱ ጮኸ፤ “እናንተ የሴኬም ሰዎች! እኔን ብታዳምጡኝ እግዚአብሔርም እናንተን ያዳምጣችኋል።
እግዚአብሔርን ብትፈሩና ብታመልኩት፥ ቃሉንም ብታዳምጡ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ብትጠብቁ፥ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትከተሉ ሁሉ ነገር ይሠምርላችኋል፤
ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባታዳምጡ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር ቅጣት ይበረታባችኋል፤