እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ እኔ በደረስኩበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር በረከትን ሰጥቶሃል፤ የምሠራውስ መቼ ለቤተሰቤ የሚጠቅም ነገር ነው?” አለው።
1 ጢሞቴዎስ 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለራሱ ዘመዶች፥ ይልቁንም ለቅርብ ቤተሰቦቹ የማያስብ ሃይማኖቱን የካደ ነው፤ እንዲያውም ከማያምን ሰው እንኳ የባሰ ክፉ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ዘመዶቹን፣ በተለይም የቅርብ ቤተ ሰቡን የማይረዳ ከሆነ ሃይማኖቱን የካደ፣ ከማያምንም ሰው ይልቅ የባሰ ክፉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ቢሆን ግን ለገዛ ዘመዶቹ በተለይም ለቤተ ሰቡ አባላት የማያስብ ከሆነ፥ እምነትን የካደና ከማያምን ሰው ይልቅ የባሰ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው። |
እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ እኔ በደረስኩበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር በረከትን ሰጥቶሃል፤ የምሠራውስ መቼ ለቤተሰቤ የሚጠቅም ነገር ነው?” አለው።
ምግባችሁን ከተራበ ሰው ጋር እንድትካፈሉ፥ ማደሪያ የሌለውን ድኻ በቤታችሁ እንድትቀበሉ፥ የተራቈቱትን እንድታለብሱ፥ ከቅርብ ዘመዶቻችሁም ራሳችሁን እንዳትደብቁ አይደለምን?
እነርሱንም አልሰማም ቢል ለቤተ ክርስቲያን ንገር፤ ቤተ ክርስቲያንንም የማይሰማ ከሆነ እንደ አረመኔና ተጸጽቶ እንደማይመለስ ኃጢአተኛ ቊጠረው።
እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፥ ለልጆቻችሁ መልካም ነገር መስጠትን ካወቃችሁ፤ ታዲያ፥ በሰማይ ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን አይሰጣቸውም!
ወደ እናንተ ለመምጣት ስዘጋጅ አሁን ሦስተኛዬ ጊዜዬ ነው፤ እኔ ሸክም ልሆንባችሁ አልፈልግም፤ እኔ የምፈልገው እናንተን እንጂ ገንዘባችሁን አይደለም። ለልጆቻቸው ሀብት ማከማቸት የሚገባቸው ወላጆች ናቸው እንጂ ልጆች ለወላጆቻቸው ሀብት አያከማቹም።
“እግዚአብሔርን እናውቃለን” ይላሉ፤ በሥራቸው ግን ይክዱታል፤ እነርሱ አጸያፊዎች፥ የማይታዘዙና ምንም መልካም ሥራ ማድረግ የማይችሉ ናቸው።
ነገር ግን በቀድሞ ዘመን በሕዝቡ መካከል ሐሰተኞች ነቢያት እንደ ነበሩ፥ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር እንዲሠራጭ ያደርጋሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ።
የሚፈረድባቸው መሆኑ ከብዙ ጊዜ በፊት የተጻፈባቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እናንተ ሾልከው ገብተዋል፤ እነርሱ የአምላካችንን ጸጋ በስድነት የሚለውጡ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ናቸው፤ እርሱ ብቻ ገዢአችንና ጌታችን የሆነን ኢየሱስ ክርስቶስንም ይክዳሉ።
አንተ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ስፍራ መኖርህን ዐውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል፤ በእኔ ላይ ያለህን እምነት አልካድክም፤ ታማኝ ምስክሬ የነበረው አንቲጳስ ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ ከተማ በተገደለ ጊዜ እንኳ በእኔ ማመንህን አልተውክም።
ሥራህን ዐውቃለሁ፤ እነሆ፥ ማንም ሊዘጋው የማይችለውን የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌልሃለሁ፤ ኀይልህ ትንሽ መሆኑን ዐውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ ቃሌን ጠብቀሃል፤ ስሜንም አልካድክም።