1 ጢሞቴዎስ 5:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚህን ዓለም ደስታ ብቻ የምትወድ መበለት ግን በቁሟ የሞተች ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድራዊ ደስታን የምትሻዋ መበለት ግን በሕይወት ብትኖርም የሞተች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዚህ ዓለም ደስታ የምትኖር መበለት ግን በሕይወትዋ ሳለች እንኳ የሞተች ናት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት። |
እናንተ ግን ጥሪውን በመቀበል ፈንታ በዓል አደረጋችሁ፤ የምትበሉትንም በግና በሬ ዐረዳችሁ፤ ወይን ጠጅም ጠጥታችሁ “ነገ እንሞታለን ዛሬ እንብላ እንጠጣ!” አላችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በማንም ያልተደፈርሽ የባቢሎን ከተማ ሆይ! ወርደሽ በዐቧራ ላይ ተቀመጪ፤ ወርደሽ በዙፋን ላይ ሳይሆን፤ በመሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅምጥልና ለስላሳ መባልሽ ይቀራል።
ቀደም ብለው ምርጥ ምግብ ይመገቡ የነበሩት፥ አሁን በመንገድ ላይ ወድቀዋል። ሐምራዊ ልብስ ለብሰው ያደጉት አሁን በዐመድ ክምር ላይ ተጋደሙ።
ከዚህም በኋላ ራሴን፦ እነሆ፥ ለብዙ ዓመት የሚበቃህ ብዙ ሀብት አለህ፤ እንግዲህ ዕረፍት በማድረግ ተዝናና! ብላ! ጠጣ! ደስ ይበልህ! እለዋለሁ’ አለ።
ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? የተዋበ ልብስ የለበሰውን ሰው ለማየት ነውን? የተዋበ ልብስ የሚለብሱና በድሎት የሚኖሩማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ፤
በመካከላችሁ በመለሳለስና በቅምጥልነት በትውልዱም በመመካት የሚኖረው ሰው እንኳ ለወንድሙ፥ ዐቅፋው ለምትተኛው ሚስቱና ከጥፋት ለተረፉት ልጆቹ ከዚያ ምግብ ለመስጠት ይሰስታል።
በመለሳለስና በቅምጥልነት በመካከልህ የምትኖር በትውልድዋ የምትመካና ከመለስለስዋ ብዛት እግሮችዋ መሬት ረግጠው የማያውቁ ዐቅፋው ከምትተኛው ባልዋና ከልጆችዋ ትሰስታለች።
ኃጢአት በመሥራታችሁና የኃጢአተኛው ሥጋችሁ በክርስቶስ በማመን ባለመገረዙ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አድርጓችኋል፤ ኃጢአታችሁንም ሁሉ ይቅር ብሎላችኋል።
እነዚህ ሰዎች በየቤቱ ሾልከው እየገቡ ብዙ ኃጢአት የተከመረባቸውንና በልዩ ልዩ ፍትወት የሚመሩ መንፈሰ ደካማ የሆኑ ሴቶችን እንደሚያጠምዱት ሰዎች ናቸው።
እርስዋ ለራስዋ ክብርንና ምቾትን የሰጠችውን ያኽል ሥቃይና ሐዘን ስጡአት፤ እርስዋ በልብዋ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ከቶ አይደርስብኝም’ በማለት ትመካለች።
“ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ሰባቱን የእግዚአብሔር መንፈሶችና ሰባቱን ኮከቦች ከያዘው የተነገረ ነው፤ ሥራህን ዐውቃለሁ፤ በስም ሕያው ነህ፤ ነገር ግን ሞተሃል።
ሳሙኤልም “ንጉሥ አጋግን ወደዚህ አምጣልኝ!” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ አጋግም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ ወደ እርሱ መጣ፤ በልቡም “ሞት እንዴት መራራ ናት!” እያለ ያስብ ነበር፤
ለናባልም ይነግሩት ዘንድ እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጣቸው፦ “ሰላም ላንተ፥ ሰላም ለቤትህ፥ ሰላም ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን ብላችሁ ሰላምታ አቅርቡለት።