1 ጢሞቴዎስ 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ዲያቆናት የተከበሩና በቃላቸው የሚጸኑ፥ ብዙ የወይን ጠጅ የማይጠጡ፥ ለገንዘብ የማይስገበገቡ መሆን አለባቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዲያቆናትም እንደዚሁ የተከበሩ፣ ቃላቸውን የማይለዋውጡ፣ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጐመጁ፣ ያለ አግባብ የሚገኝ ጥቅምንም የማያሳድዱ ሰዎች መሆን ይገባቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ዲያቆናት መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው፥ ቃላቸውን የማያጥፉ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለገንዘብ የማይስገበገቡ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለነውረኛ ረብ የማይስገበገቡ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ |
ጠላቶቼ የሚናገሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ ስለ ሆነ፥ ከአፋቸው እውነት አይገኝም፤ ሐሳባቸውም በተንኰል የተሞላ ነው፤ ጒሮሮአቸውም እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም ሰውን ይሸነግላሉ።
“አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ ጠጥታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን እንዳትገቡ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ትሞታላችሁ፤ ይህም ሕግ ከእናንተ በኋላ በሚነሣውም ትውልድ ዘንድ ሁሉ ተጠብቆ መኖር አለበት።
ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ከተማ ለሚኖሩ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፥ እንዲሁም ለኤጲስ ቆጶሳትና ዲያቆናት፦
ስለዚህ አንድ ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) ነቀፋ የሌለበት፥ አንዲት ሚስት ብቻ ያገባ፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚገዛ፥ በሥርዓት የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ችሎታ ያለው፥
ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) የእግዚአብሔርን ሥራ በዐደራ የተቀበለ ስለ ሆነ የማይነቀፍ መሆን አለበት፤ እንዲሁም የማይኰራ፥ በቶሎ የማይቈጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ መሆን አለበት።
እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በጠባያቸው የተከበሩ እንዲሆኑ እንጂ ሐሜተኞችና፥ የመጠጥ ሱሰኞች እንዳይሆኑና መልካሙን ትምህርት እንዲያስተምሩ ምከራቸው።
በዐደራ የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ መንጋውን የምትጠብቁትም በግድ ሳይሆን እግዚአብሔር በሚፈልገው ዐይነት፥ በፈቃደኛነት ይሁን፤ ለገንዘብ በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ፍላጎት ይሁን።