1 ጢሞቴዎስ 3:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ሚስቶቻቸው የተከበሩ፥ ሰውን የማያሙ፥ በመጠን የሚኖሩ፥ በሁሉም ነገር ታማኞች መሆን ይገባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁ ሴቶችም የተከበሩ፣ ሐሜተኞች ያልሆኑ ነገር ግን ልከኞችና በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ሴቶች መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው፥ ሐሜተኞች ያልሆኑ፥ በመጠን የሚኖሩ፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ሴቶች ጭምቶች፥ የማያሙ፥ ልከኞች፥ በነገር ሁሉ የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል። |
እያንዳንዱ ከባልንጀራው ተንኰል ይጠንቀቅ፤ ወንድሙን እንኳ ቢሆን ማመን የለበትም፤ ወንድም የተባለ ሁሉ (እንደ ያዕቆብ) አታላይ ሆኖአል፤ ወዳጅ የተባለም ሁሉ የባልንጀራውን ስም ያጠፋል።
ካህን የሆነ ሁሉ ባልዋ የሞተባትን ወይም ከባልዋ የተፋታችውን ሴት ማግባት አይፈቀድለትም፤ ነገር ግን ድንግል የሆነችውን እስራኤላዊት ልጃገረድ ወይም ካህን የሆነ ባልዋ የሞተባትን ሴት ማግባት ይችላል።
ካህናት ለአምላካቸው ተለይተው የተቀደሱ ስለ ሆኑ፥ አመንዝራ የነበረች ሴት፥ ወይም ክብረ ንጽሕናዋ የተደፈረ ልጃገረድ ወይም አግብታ የፈታች ሴት አያግቡ፤
ስለዚህ በበደል፥ በክፋት፥ በሥሥት፥ በተንኰል፥ በምቀኝነት፥ በነፍሰገዳይነት፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በክፉ ምኞት ሁሉ የተሞሉ፥ እንዲሁም ሐሜተኞች ናቸው፤
ስለዚህ አንድ ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) ነቀፋ የሌለበት፥ አንዲት ሚስት ብቻ ያገባ፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚገዛ፥ በሥርዓት የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ችሎታ ያለው፥
ጌቶቻቸው አማኞች የሆኑ አገልጋዮች በጌታ ኢየሱስ ወንድሞቻቸው ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ይልቅስ ከአገልግሎታቸው ጥቅም የሚያገኙ ጌቶቻቸው አማኞችና የተወደዱ ወንድሞቻቸው ስለ ሆኑ ከበፊት ይበልጥ ያገልግሉአቸው። አንተም ማስተማርና መምከር የሚገባህ ይህን ነው።
እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በጠባያቸው የተከበሩ እንዲሆኑ እንጂ ሐሜተኞችና፥ የመጠጥ ሱሰኞች እንዳይሆኑና መልካሙን ትምህርት እንዲያስተምሩ ምከራቸው።