1 ጢሞቴዎስ 1:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን ለአገልግሎት በመሾም ታማኝ አድርጎ የቈጠረኝንና የሰጠኝን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአገልግሎቱ በመሾም ታማኝ አድርጎ የቈጠረኝን፣ ብርታትም የሰጠኝን ጌታችንን ክርስቶስ ኢየሱስን አመሰግናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ብርታት የሰጠኝን ጌታችንን ክርስቶስ ኢየሱስን አመሰግናለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኀይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቍኦጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤ |
ይህንንም ያደረገው ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ፥ እንዲሁም ወልድን እንዲያከብሩ ነው፤ ወልድን የማያከብር፥ ወልድን የላከውን አብን አያከብርም።
እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን።
ጌታም ሐናንያን እንዲህ አለው፦ “እርሱ ስሜን ለአረማውያን፥ ለነገሥታትና ለእስራኤል ሰዎች የሚያሳውቅ፥ የእኔ ምርጥ መሣሪያ ስለ ሆነ ወደ እርሱ ሂድ፤
ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።
ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? እነርሱ እናንተ እንድታምኑ ያደረጉአችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ እያንዳንዳቸው የሚያገለግሉትም ጌታ ለያንዳንዳቸው በመደበላቸው ሥራ ነው፤
ስላላገቡ ሰዎች ከጌታ የተቀበልኩት ትእዛዝ የለኝም፤ ነገር ግን በጌታ ምሕረት እምነት የሚጣልብኝ እንደ መሆኔ መጠን የራሴ ሐሳብ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው፤
እውነተኛው ትምህርት ግን የሚገኘው ስለተመሰገነው እግዚአብሔር ከሚያበሥረው ክቡር ወንጌል ነው፤ ይህም ወንጌል ለእኔ በዐደራ የተሰጠኝ ነው።