1 ሳሙኤል 5:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም የአሽዶድን ሕዝብ በብርቱ አስጨነቃቸው፤ እነርሱንና በዙሪያቸው ያሉትን ሕዝብ ሁሉ በእባጭ መቅሠፍት ቀጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር እጅ በአሽዶድ ሕዝብና በአካባቢዋ ላይ ጠነከረ፤ እርሱም ጥፋት አመጣባቸው፤ በዕባጭም መታቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ እጅ በአሸዶድ ሕዝብና በአካባቢዋ ላይ ጠነከረ፤ እርሱም ጥፋት አመጣባቸው፤ በዕባጭም መቅሠፍት መታቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፤ ክፉም ነገር አመጣችባቸው፤ በእነርሱም ላይ በመርከቦች ውስጥ ወጣ፤ የአዛጦንንና የአውራጃዎችዋንም ሰዎች የውስጥ አካላቸውን በዕባጭ መታ፤ በከተሞቻቸውም መካከል አይጦች ወጡ፤ በከተማውም ታላቅ መቅሠፍት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፥ አጠፋቸውም፥ አዛጦንንና ድንበራቸውንም በእባጭ መታቸው። |
የእግዚአብሔር እጅ በመስክ የሚገኘውን መንጋህን ማለት ፈረሶችህን፥ አህዮችህን፥ ግመሎችህን፥ የቀንድ ከብቶችህን፥ በጎችህንና ፍየሎችህን በታላቅ መቅሠፍት ይመታል።
አሁንም እነሆ፥ የጌታ እጅ ይመታሃል፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ ለጥቂት ጊዜም የፀሐይን ብርሃን አታይም።” ወዲያውኑ ዐይኖቹን ጭጋግና ጨለማ ሸፈናቸው፤ እጁን ይዞ የሚመራውንም ሰው ዙሪያውን መፈለግ ጀመረ።
እንደገና ወደ ፍልስጥኤማውያን ነገሥታት ሁሉ መልእክተኞች ልከው “እኛንና ቤተሰባችንን ሁሉ ከመፍጀቱ በፊት የእስራኤልን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ስፍራው መልሳችሁ ላኩ” አሉ፤ እግዚአብሔር በብርቱ ስለ ቀጣቸው በመላ ከተማይቱ የሚያስጨንቅ የሞት ፍርሀት ነበር፤
የአሽዶድ ኗሪዎች የሆነውን ነገር ሁሉ ባዩ ጊዜ “ቊጣው በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ስለ በረታ የእስራኤል አምላክ ታቦት እዚህ እኛ ዘንድ መቈየት የለበትም” አሉ።
ነገር ግን የቃል ኪዳኑ ታቦት እዚያ ከደረሰ በኋላ እግዚአብሔር ያቺንም ከተማ ጭምር ቀጣ፤ ሕዝብዋንም በብርቱ አስጨነቀ። ሕፃኑንም ሽማግሌውንም ሳይለይ ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት በእብጠት በሽታ ቀጣቸው፤