1 ሳሙኤል 5:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ነገር ግን የቃል ኪዳኑ ታቦት እዚያ ከደረሰ በኋላ እግዚአብሔር ያቺንም ከተማ ጭምር ቀጣ፤ ሕዝብዋንም በብርቱ አስጨነቀ። ሕፃኑንም ሽማግሌውንም ሳይለይ ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት በእብጠት በሽታ ቀጣቸው፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱት በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በዕባጭ መታ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱትም በኋላ የጌታ እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በእባጭ መቅሠፍት መታ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ከሄደችም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከትም ሆነ፤ የከተማዪቱንም ሰዎች ታላቁንም ታናሹንም መታ፤ የውስጥ አካላቸውንም በእባጭ መታቸው፤ የጌት ሰዎችም የውስጥ አካላቸውን ምስል ሠሩ፥ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ከተሸከሙትም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በታላቅ ድንጋጤ በከተማይቱ ላይ ሆነች፥ ከታናሹም እስከ ታላቁ ድረስ የከተማይቱን ሰዎች መታ፥ እባጭም መጣባቸው። Ver Capítulo |