“እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።
1 ሳሙኤል 31:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን በጊልቦዓ ተራራ ከእስራኤላውያን ጋር ጦርነት ገጠሙ፤ ብዙ እስራኤላውያንም ሸሹ፤ ብዙዎችም ተገደሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ወጉ፤ እስራኤላውያንም ከፊታቸው ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ተወግተው ወደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ወጉ፤ እስራኤላውያንም ከፍልስጥኤማውያን ፊት፥ በጊልቦዓ ተራራ ላይ የወደቁትን ጥለው ሸሹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ተዋግተውም በጌላቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፥ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ተወግተውም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወደቁ። |
“እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።
ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ነበርኩ፤ ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ የጠላት ሠረገሎችና ፈረሰኞች ወደ እነርሱ ሲጠጉ አየሁ፤
ሌላው የሳኦል ዘር የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ሲሆን፥ እርሱ ሳኦልና ዮናታን በተገደሉ ጊዜ ገና የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፤ የእነርሱን ሞት የሚገልጠው ወሬ ከኢይዝራኤል ከተማ በተነገረ ጊዜ ሞግዚቱ እርሱን ይዛ ሸሸች፤ ነገር ግን በጥድፍያ በምትሸሽበት ጊዜ ከእጅዋ ወደቀ፤ ከዚህም የተነሣ ሽባ ሆነ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት የጦር ሠራዊታቸውን ሰበሰቡ፤ አኪሽም ዳዊትን “አንተና ተከታዮችህ ከእኔ ጐን ተሰልፋችሁ መዋጋት እንደሚገባችሁ በእርግጥ ዕወቅ” አለው።
ሳሙኤልም ሳኦልን “ዕረፍት የምትነሣኝ ስለምንድን ነው? ስለምንስ ከመቃብር እንድነሣ አስጠራኸኝ?” አለው። ሳኦልም “እነሆ፥ እኔ በታላቅ ችግር ላይ ነኝ! ፍልስጥኤማውያን ከእኔ ጋር ጦርነት በማድረግ ላይ ናቸው፤ እግዚአብሔርም እኔን ትቶኛል፤ በነቢይም ሆነ በሕልም መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም፤ ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ትነግረኝ ዘንድ እንድትነሣ አስጠራሁህ” ሲል መለሰ።
ስለዚህ እርሱ አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣችኋል፤ ነገ አንተና ልጆችህ እኔ ወዳለሁበት ቦታ ትመጣላችሁ፤ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ሠራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”
እስራኤላውያን በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ በሚገኘው ምንጭ አጠገብ ሰፍረው ሳሉ፥ ፍልስጥኤማውያን ወታደሮቻቸውን በአንድነት ሰብስበው በማምጣት በአፌቅ አሰለፉ፤