ዳዊት፥ ንጉሥ ሳኦልን ለመውጋት ከፍልስጥኤማውያን ጋር በዘመተ ጊዜ ከምናሴ ነገድ የሆኑ ጥቂት ወታደሮች ከዳዊት ጋር ለመተባበር ሄዱ፤ ሆኖም የፍልስጥኤማውያን መሪዎች “ዳዊት እኛን ከድቶ ወደ ቀድሞ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል” ብለው ስለ ፈሩ ከተመካከሩ በኋላ ወደ ቲግላግ እንዲመለስ አደረጉት፤
1 ሳሙኤል 29:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የፍልስጥኤም ጦር አዛዦች በአኪሽ ላይ ተቈጥተው እንዲህ አሉት፤ “ይህን ሰው ቀድሞ ወደ ሰጠኸው ከተማ መልሰው፤ ከእኛ ጋር አብሮ እንዲዘምት አታድርግ፤ ጦርነቱ በሚፋፋምበት ወቅት በእኛ ላይ ሊነሣ ይችላል፤ እርሱ ከጌታው ጋር ለመስማማት የእኛን ሰዎች ከመግደል ሌላ ምን አማራጭ ይኖረዋል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን በአንኩስ ላይ ተቈጥተው እንዲህ አሉ፤ “ይህን ሰው ወደዚያው ወደ ሰጠኸው ቦታ ይመለስ ዘንድ ስደደው፤ በውጊያው ጊዜ በእኛ ላይ ተመልሶ ጠላት እንዳይሆን፣ ዐብሮን ወደ ጦርነቱ መሄድ የለበትም፤ የእኛን ሰዎች ራስ ቈርጦ ካልወሰደ ከጌታው ጋራ እንዴት ሊታረቅ ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን በአኪሽ ላይ ተቆጥተው እንዲህ አሉ፤ “ይህን ሰው እንዲመለስ አድርግ፤ ወደ ሰጠኸው ቦታ ይመለስ ዘንድ ስደደው፤ በውጊያው ላይ ተመልሶ ጠላት እንዳይሆን ከእኛ ጋር አይወርድም። እዚህ ያሉትን የእኛን ሰዎች ራስ ቆርጦ ካልወሰደ በስተቀር፥ ከጌታው ጋር እንዴት ሊታረቅ ይችላል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን በእርሱ ላይ ተቈጥተው፥ “ይህን ሰው ወደ አመጣህበት ቦታ መልሰው፤ በሰልፉም ውስጥ ጠላት እንዳይሆነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይውረድ፤ ከጌታው ጋር በምን ይታረቃል? የእነዚህን ሰዎች ራስ በመቍረጥ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን ተቆጥተው፦ ይህ ሰው ባስቀመጥኸው ስፍራ ይቀመጥ ዘንድ ይመለስ፥ በሰልፍ ውስጥ ጠላት እንዳይሆነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይውረድ፥ ከጌታው ጋር በምን ይታረቃል? የእነዚህን ሰዎች ራስ በመቁረጥ አይደለምን? |
ዳዊት፥ ንጉሥ ሳኦልን ለመውጋት ከፍልስጥኤማውያን ጋር በዘመተ ጊዜ ከምናሴ ነገድ የሆኑ ጥቂት ወታደሮች ከዳዊት ጋር ለመተባበር ሄዱ፤ ሆኖም የፍልስጥኤማውያን መሪዎች “ዳዊት እኛን ከድቶ ወደ ቀድሞ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል” ብለው ስለ ፈሩ ከተመካከሩ በኋላ ወደ ቲግላግ እንዲመለስ አደረጉት፤
ከምናሴ ነገድ ዳዊት በተመለሰ ጊዜ ወደ እርሱ የሄዱት ወታደሮች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ ዓድናሕ፥ ዮዛባድ፥ ይዲዕኤል፥ ሚካኤል፥ ዮዛባድ፥ ኤሊሁና ጺለታይ፤ እነዚህ ሁሉ በምናሴ ግዛት ሳሉ የሺህ አለቅነት ማዕርግ የነበራቸው ናቸው።
ከዚህም የተነሣ ከጠላቶቻችን ጋር ተባብረው ከወጉን በኋላ ከአገሪቱ አምልጠው መሄድ ይችላሉ፤ ስለዚህ ቊጥራቸው እየበዛ እንዳይሄድ ኑ፤ አንድ ዘዴ እንፈልግ።”
ጌታውም እምነት ያጐደለውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ሰዎች ይልቅ የዓለም ሰዎች በዓለማዊ ኑሮአቸው ብልኆች መሆናቸውን ያሳያል።
ከፍልስጥኤማውያን ጋር በመተባበር ወደ ጦሩ ሰፈር ሄደው የነበሩ አንዳንድ ዕብራውያንም ፍልስጥኤማውያንን ከድተው ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ተባበሩ።
አኪሽም ዳዊትን መልሶ እንዲህ አለው፦ “አንተ በእኔ አስተያየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ምንም እንከን የሌለብህ መሆኑን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ‘ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መዝመት አይችልም’ አሉ።
ዳዊትና ተከታዮቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ ሲደርሱ ዐማሌቃውያን ኔጌብንና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ በጺቅላግም ላይ አደጋ ጥለው አቃጠሉአት።