Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 27:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህም አኪሽ የጺቅላግን ከተማ ለዳዊት ሰጠው፤ በዚህም ምክንያት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጺቅላግ የይሁዳ ነገሥታት ይዞታ እንደ ሆነች ቀረች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ በዚያ ዕለት አንኩስ ጺቅላግን ሰጠው፤ ጺቅላግም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የይሁዳ ነገሥታት ይዞታ ሆነች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ስለዚህ በዚያ ዕለት አኪሽ ጺቅላግን ከተማ ሰጠው፤ ጺቅላግም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የይሁዳ ነገሥታት ይዞታ ሆነች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በዚ​ያም ቀን አን​ኩስ ሴቄ​ላ​ቅን ሰጠው፤ ስለ​ዚ​ህም ሴቄ​ላቅ እስከ ዛሬ ድረስ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ሆነች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በዚያም ቀን አንኩስ ጺቅላግን ሰጠው፥ ስለዚህም ጺቅላግ እስከ ዛሬ ድረስ ለይሁዳ ነገሥታት ሆነች።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 27:6
12 Referencias Cruzadas  

ሳኦል ከሞተ በኋላ ዳዊት ዐማሌቃውያንን ድል አድርጎ ተመለሰ፤ በጺቅላግም ሁለት ቀን ቈየ፤


ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በጺቅላግ በነበረ ጊዜ ከእርሱ ጋር የተቀላቀሉት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም መካከል የጦር ጀግኖች ነበሩባቸው።


ከምናሴ ነገድ ዳዊት በተመለሰ ጊዜ ወደ እርሱ የሄዱት ወታደሮች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ ዓድናሕ፥ ዮዛባድ፥ ይዲዕኤል፥ ሚካኤል፥ ዮዛባድ፥ ኤሊሁና ጺለታይ፤ እነዚህ ሁሉ በምናሴ ግዛት ሳሉ የሺህ አለቅነት ማዕርግ የነበራቸው ናቸው።


በቱኤል፥ ሖርማ፥ ጺቅላግ፥


በጺቅላግ ከተማም በተለይ በመኮናና በአካባቢዋ በሚገኙት መንደሮች፥


ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥


ጺቅላግ፥ ቤትማርካቦት፥ ሐጻርሱሳ፥


እርሱ ለሕይወቱ ሳይሳሳ በመጋፈጥ ጎልያድን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም ይህን ባየህ ጊዜ ደስ ብሎህ ነበር፤ ታዲያ አሁን አንተ በንጹሕ ሰው ላይ በደል ለመሥራት ስለምን ታስባለህ? ምክንያት በሌለውስ ነገር ዳዊትን ለመግደል ስለምን ፈለግኽ?”


ዳዊትም ንጉሥ አኪሽን “የምትወደኝ ከሆንክ በአንድ ትንሽ ከተማ እንድኖር ፍቀድልኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ በመናገሻ ከተማ ከአንተ ጋር መኖር አይገባኝም” አለው።


ነገር ግን የፍልስጥኤም ጦር አዛዦች በአኪሽ ላይ ተቈጥተው እንዲህ አሉት፤ “ይህን ሰው ቀድሞ ወደ ሰጠኸው ከተማ መልሰው፤ ከእኛ ጋር አብሮ እንዲዘምት አታድርግ፤ ጦርነቱ በሚፋፋምበት ወቅት በእኛ ላይ ሊነሣ ይችላል፤ እርሱ ከጌታው ጋር ለመስማማት የእኛን ሰዎች ከመግደል ሌላ ምን አማራጭ ይኖረዋል?


ዳዊትና ተከታዮቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ ሲደርሱ ዐማሌቃውያን ኔጌብንና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ በጺቅላግም ላይ አደጋ ጥለው አቃጠሉአት።


ይህም ከመሆኑ በፊት በይሁዳ ደቡብ የምትገኘውን የከሪታውያንን ግዛትና የካሌብን ግዛት በመውረር ጺቅላግን አቃጥለናታል” ሲል መለሰለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos