ዳዊትም ዐማሌቃዊውን “ይህን ጥፋት በራስህ ላይ ያመጣህ አንተው ራስህ ነህ፤ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ገድያለሁ ብለህ በተናገርክ ጊዜ በራስህ ላይ ፈርደሃል” አለው።
1 ሳሙኤል 25:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም የናባልን መሞት በሰማ ጊዜ “እኔን በመስደቡ እግዚአብሔር ናባልን ስለ ተበቀለውና እኔንም ከስሕተት ስለ ጠበቀኝ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱ ናባልን ስለ ክፉ ሥራው ቀጥቶታል” አለ። ከዚህም በኋላ ዳዊት ወደ አቢጌል መልእክተኛ ልኮ ሊያገባት መፈለጉን ገለጠላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ናባል መሞቱን በሰማ ጊዜ፣ “የናባልን ስድብ የተበቀለልኝና እኔን አገልጋዩን ክፉ ከማድረግ የጠበቀኝ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ናባል የሠራውንም ክፉ ነገር በራሱ ላይ መለሰበት” አለ። ዳዊትም አቢግያ ሚስት ትሆነው ዘንድ በመጠየቅ መልእክት ላከባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ናባል መሞቱን በሰማ ጊዜ፥ “የናባልን ስድብ የተበቀለልኝና እኔን አገልጋዩን ክፉ ከማድረግ የጠበቀኝ ጌታ ይመስገን፤ ናባል የሠራውንም ክፉ ነገር በራሱ ላይ መለሰበት” አለ። ዳዊትም አቢጌል ሚስት ትሆነው ዘንድ በመጠየቅ መልእክት ላከባት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ናባል እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ “ከናባል እጅ የስድቤን ፍርድ የፈረደልኝ፥ ባሪያውንም ከክፉዎች እጅ የጠበቀ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እግዚአብሔርም የናባልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰ” አለ። ዳዊትም ያገባት ዘንድ አቤግያን እንዲያነጋግሩለት ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ናባል እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፦ ከናባል እጅ የስድቤን ፍርድ የፈረደልኝ፥ ባሪያውንም ከክፋት የጠበቀ እግዚአብሔር ይመስገን፥ እግዚአብሔርም የናባልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰ አለ። ዳዊትም ልኮ ያገባት ዘንድ አቢግያን ተነጋገራት። |
ዳዊትም ዐማሌቃዊውን “ይህን ጥፋት በራስህ ላይ ያመጣህ አንተው ራስህ ነህ፤ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ገድያለሁ ብለህ በተናገርክ ጊዜ በራስህ ላይ ፈርደሃል” አለው።
ነገር ግን አስቴር ወደ ንጉሡ ቀረበች፤ ንጉሡም ትእዛዙን በጽሑፍ እንዲተላለፍ አደረገ፤ ያም ትእዛዝ ባስገኘው ውጤት ሃማን አይሁድን ለመደምሰስ ዐቅዶት የነበረው ሤራ በራሱ ላይ እንዲመለስበት ሆነ፤ እርሱና ዐሥር ልጆቹ በእንጨት ላይ ተሰቀሉ።
እግዚአብሔርን በድዬዋለሁ፤ ስለዚህም እርሱ የቀረበብኝን ክስ ተመልክቶ እስኪፈርድልኝ ድረስ ቊጣውን እታገሣለሁ፤ በመጨረሻም እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤ ፍትሕንም ይሰጠኛል።
ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም ምንም እንኳ እኛ ብቁዎች ሆነን ሳንታይ ብንቀር እናንተ ዘወትር መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው እንጂ የእኛን ብቃት ለማሳየት አይደለም።
ራሱ የሰላም አምላክ በሁሉ ነገር ይቀድሳችሁ፤ መንፈሳችሁ፥ ነፍሳችሁ፥ አካላችሁ በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚመጣበት ቀን ያለ ነቀፋ ተጠብቆ ይኑር።
እግዚአብሔር ይፍረድ፤ ከሁለታችንም ስሕተተኛው ማን እንደ ሆነ እርሱ ይወስን፤ እግዚአብሔር ይህን ጉዳይ ተመልክቶ ይከላከልልኝ፤ ከአንተም እጅ ያድነኝ።”
የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤
በአንቺ ላይ ጒዳት ከማድረስ እግዚአብሔር ጠብቆኛል፤ ፈጥነሽ ወደ እኔ ባትመጪ ኖሮ ግን፥ ከናባል ወንዶች አንድ እንኳ ሳላስተርፍ ከንጋት በፊት ሁሉንም ለመግደል በሕያው እግዚአብሔር ስም ምዬ ነበር።”
በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ራሱ ሳኦልን ይገድለዋል፤ የሚሞትበት ጊዜ ደርሶ፥ አለበለዚያም በጦርነት መሞቱ አይቀርም፤