1 ሳሙኤል 24:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ወግቶ ከተመለሰ በኋላ ዳዊት በዔንገዲ አጠገብ በሚገኘው ምድረ በዳ የሚገኝ መሆኑን ሰማ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ከተመለሰ በኋላ፣ “እነሆ፤ ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ከዚያ ወደ ላይ ወጥቶ በዔንገዲ ምሽጎች ተቀመጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከዚያ መጥቶ በዓይን ጋዲ በጠባብ ቦታ ተቀመጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ከተመለሰ በኋላ፦ እነሆ፥ ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ አለ የሚል ወሬ ደረሰለት። |
ከእናንተ አንዳንዶቹ ሌሎችን ለማስገደል ሐሰት ይናገራሉ፤ አንዳንዶቹ ለጣዖት የተሠዋውን ሁሉ ይመገባሉ፤ አንዳንዶቹ ዘወትር ፍትወታቸውን ለማርካት ይጣደፋሉ።
ከዔንገዲ ጀምሮ እስከ ዔንዔግላይም ድረስ ዓሣ አጥማጆች ይቆማሉ፤ ያም ቦታ መረቦች የሚዘረጉበት ቦታ ይሆናል፤ በሜዲትራኒያን ባሕር እንደሚገኘው ዐይነት በዚህም ልዩ ልዩ ዓሣ ይገኛል።
ከዚፍ ነዋሪዎች አንዳንዶቹ በጊብዓ ወደሚገኘው ወደ ሳኦል ሄደው እንዲህ አሉ፥ “ዳዊት በእኛ ግዛት ውስጥ ከይሁዳ ምድረ በዳ በስተ ደቡብ ባለው በሐኪላ ተራራ ላይ በምትገኘው በሖሬሽ ተሸሽጎ ይገኛል።