1 ሳሙኤል 21:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ዘንድ እንዲያብድ ወደ እኔ ይህን ሰው ያመጣችሁት፥ እኔ እብድ አጥቼ ነውን? ይህ ሰው ወደ ቤቴ መግባት አለበትን?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፊቴ እንዲህ ይሆን ዘንድ ይህን ሰው እዚህ ያመጣችሁት እብድ ዐጥቼ ነውን? እንዲህ ያለውስ ሰው ወደ ቤቴ መግባት ይገባዋልን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊቴ እንዲህ ይሆን ዘንድ ይህን ሰው እዚህ ያመጣችሁት እብድ አጥቼ ነውን? እንዲህ ያለውስ ሰው ወደ ቤቴ መግባት ይገባዋልን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቴ ያብድ ዘንድ ይህን ያመጣችሁት እኔ የእብዶች አለቃ ነኝን? እንዲህ ያለውስ ወደ ቤቴ ይገባልን?” አላቸው። |
ዳዊት ከጋት ከተማ ሸሽቶ በዐዱላም ከተማ አጠገብ ወደሚገኝው ወደ አንድ ዋሻ ሄደ፤ ወንድሞቹና ሌሎቹም ቤተሰቦቹ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ሄደው ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤