የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤
1 ሳሙኤል 20:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ፍላጻዎቹን እንዲያመጣ ልጁን እልካለሁ፤ ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ ወደዚህ ናቸውና አምጣቸው!’ ካልሁት አንተ ከተደበቅኽበት ቦታ ልትወጣ ትችላለህ፤ ስለዚህ ምንም ችግር እንደማይደርስብህና ምንም አደጋ እንደሌለ በእግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ ‘ሂድና ፍላጾቹን አምጣቸው’ ብዬ አንድ ልጅ እልካለሁ፤ ልጁንም፣ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት፣ ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ሄደህ አምጣቸው’ ያልሁት እንደ ሆነ፣ ሕያው እግዚአብሔርን! ክፉ ነገር አያገኝህም፤ አደጋም የለም፤ ውጣና ና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም፥ ‘ሂድና ፍላጾቹን አምጣቸው’ ብዬ አንድ ልጅ እልካለሁ፤ ልጁንም፥ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት፥ ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ሄደህ አምጣቸው’ ያልሁት እንደሆነ፥ በሕያው ጌታ ስም! ክፉ ነገር አያገኝህም፤ ውጣና ና፤ አደጋ እንደማይኖርም እምልልሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፦ ሂድ ፍላጻዎቹን ፈልግ ብዬ ብላቴናውን እልካለሁ፤ ብላቴናውንም፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ይዘኸው ወደ እኔ ና ያልሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለብህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፦ ሂድ ፍላጻዎችን ፈልግ ብዬ ብላቴናውን እልከዋለሁ፥ ብላቴናውንም፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወደዚህ ነው፥ ይዘኸው ወደ እኔ ና ያልሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ደኅንነት ነውና ምንም የለብህም። |
የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤
‘አሺማ’ ተብላ በምትጠራ በሰማርያ ሴት አምላክ የሚምሉ ‘በዳን አምላክ’ ወይም ‘በቤርሳቤህ አምላክ’ እያሉ የሚምሉ ሁሉ ይወድቃሉ፤ ከወደቁበትም ፈጽሞ መነሣት አይችሉም።”
ልጁንም “ፈጥነህ ሂድና የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልገህ አምጣልኝ” አለው፤ ልጁም ሲሮጥ ዮናታን ከዚያ ልጅ ፊት አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ፤