La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 13:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ‘ፍልስጥኤማውያን ገና በጌልገላ ሳለሁ አደጋ ሊጥሉብኝ ነው የእግዚአብሔርንም ርዳታ ገና አለመንኩም’ ብዬ አሰብኩ፤ መሥዋዕት ማቅረብ እንደሚገባኝም ተረዳሁ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

‘ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንሁም’ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የጌታን ርዳታ አልለመንሁም፥ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚህ፦ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አሁን ወደ እኔ ወደ ጌል​ጌላ ይወ​ር​ዱ​ብ​ኛል፤ እኔም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት አል​ለ​መ​ን​ሁም አልሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ደፍሬ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን አሳ​ረ​ግሁ” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰለዚህ፦ ፍልስጥኤማውያን አሁን ወደ ጌልገላ ይወርዱብኛል፥ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንሁም አልሁ፥ ስለዚህም ሳልታገሥ የሚቃጠልን መሥዋዕት አሳረግሁ አለ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 13:12
9 Referencias Cruzadas  

እንዲህም በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ድንቅ ነው! ኀይልህ እጅግ ታላቅ በመሆኑ ጠላቶችህ በፍርሃት በፊትህ ይሸማቀቃሉ።


እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው በዓል ምነው ቶሎ ባለፈልን! ስንዴ ወደ ገበያ ለመውሰድ ሰንበትም መቼ ያልፍልናል? በዓላቱ ካለፉልን የእህሉን መስፈሪያ አሳንሰን ከፍተኛ ዋጋ እንጠይቃለን፤ በሐሰተኛ ሚዛንም ሕዝቡን እናታልላለን፤


ስለዚህ እግዚአብሔር የሚወደው በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለ ሆነ እያንዳንዱ ለመስጠት የፈለገውን በልቡ ፈቅዶ በደስታ ይስጥ እንጂ እያመነታ ወይም በግዴታ አይስጥ።


ሳሙኤል ግን “ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ሕዝቡ ሊከዱኝ ተቃርበው ነበር፤ አንተም በቀጠርከኝ ሰዓት ሳትመጣ ቀረህ፤ ከዚህም በላይ ፍልስጥኤማውያን መጥተው በሚክማስ ተሰለፉ፤


ሳሙኤልም ሲመልስለት እንዲህ አለው፤ “ይህ የሞኝነት አሠራር ነው፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዝ አልፈጸምክም፤ ትእዛዙን ብትፈጽም ኖሮ አንተና ዘሮችህ በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም እንድትነግሡ ዛሬ መንግሥትህን ባጸናልህ ነበር፤


በማግስቱም ማለዳ በመነሣት ሳኦልን ፈልጎ ለማግኘት ሄደ፤ ሳኦል ለራሱ ሐውልት ወዳቆመባት ወደ ቀርሜሎስ ከተማ ከደረሰ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልጌላ መሄዱን ሰማ፤


ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የሚወደው የቱን ይመስልሃል? መታዘዝን ወይስ ቊርባንና መሥዋዕት ማቅረብን? ለእርሱ መታዘዝ ምርጥ የበግ መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤


የሳኦል እረኞች አለቃ የሆነው ኤዶማዊው ዶይቅ በዚያኑ ቀን ሃይማኖታዊ ሥርዓትን ለመፈጸም በዚያ ተገኝቶ ነበር።