1 ሳሙኤል 1:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ደግሞ እርሱን ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ እንዲሆን አድርጌአለሁ፤ ስለዚህም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።” ከዚያም በኋላ በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እኔም ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።” እርሱም በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እኔም ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ለጌታ የተሰጠ ይሆናል።” እርሱም በዚያ ለጌታ ሰገደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ደግሞ ዕድሜውን ሙሉ እግዚአብሔርን ያገለግል ዘንድ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የለመንሁትን ልመናዬን ሰጥቶኛል፥ እኔም ደግሞ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል። |
ከዚህ በኋላ ለጌታዬ ልጅ ሚስት የምትሆነዋን ሴት ወዳገኘሁበት ወደ ጌታዬ ወንድም ቤት በቀና መንገድ ለመራኝ ለእግዚአብሔር በጒልበቴ ተንበርክኬ ሰገድሁ፤ የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤
ጌዴዎን ስለ ሰውየው ሕልምና ስለ ፍቹም ምንነት በሰማ ጊዜ በጒልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤላውያንም ሰፈር ተመልሶ “እግዚአብሔር በምድያማውያንና በሠራዊቱ ላይ ድልን የሚያቀዳጃችሁ ስለ ሆነ ተነሡ!” አላቸው።
ሐናም እንዲህ ስትል ስእለት ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እኔን አገልጋይህን ተመልከተኝ! መከራዬንም በማየት አስበኝ! አትርሳኝም! አንድ ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የተለየ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ጠጒሩም ከቶ አይላጭም።”
“ልጄ ጡት በሚተውበት ጊዜ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ወደሚኖርበት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወዲያውኑ እወስደዋለሁ” ብላ ለባልዋ ነግራው ስለ ነበር ሐና በዚህ ጊዜ አብራ አልወጣችም፤
ዔሊም ሕልቃናን ከሚስቱ ከሐና ጋር በሚመርቅበት ጊዜ፥ ሕልቃናን “ለእግዚአብሔር የተለየ አድርጋችሁ በሰጣችሁት በዚህ ልጅ ፈንታ ከዚህቹ ሴት ሌሎችን ልጆች ይስጥህ!” ይለው ነበር። ከዚያን በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር።
ዳዊትም “እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ የማደርገውንም አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ” ሲል መለሰለት። አኪሽም “መልካም ነው! እኔ አንተን ለዘለቄታ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ!” አለው።