1 ጴጥሮስ 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በእናንተ ኀላፊነት ሥር ያሉትን ጨቊኖ በመግዛት ሳይሆን ለመንጋው መልካም ምሳሌነትን በማሳየት ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በዐደራ ለተሰጣችሁ መንጋ መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በላያቸው በመሠልጠን አይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእናንተ ኀላፊነት ሥር ላለው ለመንጋው መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በኃይል በመግዛት አይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኀይል አትግዙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤ |
ከጥንት ጀምሮ የመረጥከውን፥ የራስህ ወገን እንዲሆን ከባርነት የዋጀኸውን ሕዝብህን አስታውስ፤ ከዚህ በፊት መኖሪያህ ያደረግኸውን የጽዮንን ተራራ አስብ።
የደከሙትን አላበረታቸሁም፤ የታመሙትን አላዳናችሁም፤ የተሰበሩትን አልጠገናችሁም፤ የባዘኑትን አልመለሳችሁም፤ የጠፉትን አልፈለጋችሁም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በግፍና በጭካኔ ገዛችኋቸው።
እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።
ነገር ግን መሠዊያውንና ከመጋረጃው በስተውስጥ በኩል ያለውን ቅድስተ ቅዱሳኑን የሚመለከተውን የክህነት አገልግሎት የምትፈጽሙ አንተና ልጆችህ ብቻ ናችሁ፤ የክህነትን አገልግሎት ዕድል ፈንታ አድርጌ ስለ ሰጠኋችሁ ይህ ሁሉ ኀላፊነት የእናንተ ነው፤ ካህን ያልሆነ ማንኛውም ሰው ወደዚያ ቢቀርብ ይሞታል።”
መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
ለመሆኑ አጵሎስ ምንድን ነው? ጳውሎስስ ምንድን ነው? እነርሱ እናንተ እንድታምኑ ያደረጉአችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ እያንዳንዳቸው የሚያገለግሉትም ጌታ ለያንዳንዳቸው በመደበላቸው ሥራ ነው፤
እኛ የምናስተምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ራሳችን ስለ ኢየሱስ የእናንተ አገልጋዮች መሆናችንን ነው እንጂ ስለ ራሳችንስ አንሰብክም።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።