በሁሉም ነገር የተመቻቸና አስተማማኝ፥ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ከእኔ ጋር ስለ ገባ፥ በውኑ ቤቴ ለእግዚአብሔር ታማኝ አይደለም? ርዳታዬና ፍላጎቴስ ሁሉ እንዲሟላ አያደርግምን?
1 ጴጥሮስ 2:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ወተት እንደሚመኙ እናንተም ለመዳን እያደጋችሁ የምትሄዱበትን ንጹሑን መንፈሳዊ ትምህርት ተመኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድነታችሁ እንድታድጉ፣ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ፥ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኵኦል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ። |
በሁሉም ነገር የተመቻቸና አስተማማኝ፥ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ከእኔ ጋር ስለ ገባ፥ በውኑ ቤቴ ለእግዚአብሔር ታማኝ አይደለም? ርዳታዬና ፍላጎቴስ ሁሉ እንዲሟላ አያደርግምን?
ተመልሰውም በእኔ ጥላ ሥር ይሆናሉ፤ እንደ እህል ቡቃያ ይለመልማሉ፤ እንደ ወይን ተክልም ያብባሉ፤ መዓዛቸውም እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ዝነኛ ይሆናል።
ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
በጥምቀት ከእርሱ ጋር በተቀበርን ጊዜ የእርሱም ሞት ተካፋዮች ሆነናል፤ ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ እኛም በአዲስ ሕይወት እንኖራለን።
ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ማመስገንም ተገቢያችን ነው፤ የምናመሰግነውም እምነታችሁ ይበልጥ እያደገና የእያንዳንዳችሁ የእርስ በርስ ፍቅር እየጨመረ በመሄዱ ነው።
ይልቅስ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እርሱንም በማወቅ ከፍ ከፍ በሉ፤ ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።