ዔሳው በዙሪያው ተመልክቶ ሴቶቹንና ልጆቹን ባየ ጊዜ “እነዚህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች የማን ናቸው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ሲል መለሰ።
1 ነገሥት 5:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኪራም የሰሎሞን መልእክት ሲደርሰው እጅግ ስለ ተደሰተ፥ “በእርሱ እግር ተተክቶ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ እንዲነግሥ ይህን የመሰለ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን!” አለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኪራም የሰሎሞን መልእክት በደረሰው ጊዜ እጅግ ደስ ስላለው፣ “ይህን ታላቅ ሕዝብ እንዲመራ ለዳዊት ጥበበኛ ልጅ ሰጥቶታልና ዛሬ ምስጋና ለእግዚአብሔር ይግባው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኪራምም የሰሎሞን መልእክት ሲደርሰው እጅግ ስለ ተደሰተ፥ “በእርሱ እግር ተተክቶ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ እንዲነግሥ ይህን የመሰለ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠ ጌታ ይመስገን!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኪራምም የሰሎሞንን ቃል ሰምቶ እጅግ ደስ አለውና፥ “በዚህ ታላቅ ሕዝብ ላይ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠ እግዚአብሔር ዛሬ ይመስገን” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኪራምም የሰሎሞንን ቃል ሰምቶ እጅግ ደስ አለውና “በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠ እግዚአብሔር ዛሬ ይመስገን፤” አለ። |
ዔሳው በዙሪያው ተመልክቶ ሴቶቹንና ልጆቹን ባየ ጊዜ “እነዚህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች የማን ናቸው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ሲል መለሰ።
‘ዛሬ ከእኔ ዘሮች መካከል አንዱ በእኔ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ ያደረገና ይህን ለማየት ያበቃኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን!’ ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ።”
አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን! እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል።”
ስለዚህ ክፉውንና በጎውን በመለየት ሕዝብህን በትክክለኛ ፍርድ ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብ ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሕዝብህን እንዴት ልመራ እችላለሁ?”
ሰሎሞን በመላው እስራኤል ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችን ሾመ፤ የእነርሱም ተግባር ከየግዛታቸው ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተሰብ ቀለብ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ማቅረብ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው።
ስለዚህ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቈርጡ ሰዎችን ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፤ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደርጋለሁ፤ ለሰዎችህም አንተ የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተ እንደምታውቀው የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቈራረጥ የአንተን ሰዎች ያኽል ዕውቀት የላቸውም።”
ከዚህ በኋላ ኪራም ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ለሰሎሞን ላከ “ያስተላለፍከው መልእክት ደርሶኛል፤ አንተ የምትፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፤ የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባውን ግንድ አዘጋጅቼ አቀርብልሃለሁ፤
እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።