1 ነገሥት 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ሰሎሞን በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ ሰሎሞን በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር። |
ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የአባቱ የሰሎሞን አማካሪዎች የነበሩትን ሽማግሌዎች በአንድነት ሰብስቦ “እንግዲህ ለዚህ ሕዝብ መልስ መስጠት እንድችል ምን ትመክሩኛላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
እነዚህ ሁሉ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ወታደሮች ዳዊትን በመላው እስራኤል ላይ ለማንገሥ ቊርጥ ውሳኔ አድርገው ወደ ኬብሮን ሄዱ፤ የቀሩትም እስራኤላውያን በዚሁ ዓላማ በአንድነት ተስማምተው ነበር፤
ሰሎሞን እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን ካለበት፥ በገባዖን ከሚገኘው ኰረብታማ ማምለኪያ ስፍራ ተነሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ በእስራኤል ላይ ነገሠ።
እንዲህም አልኳቸው፦ “የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ኃጢአት የሠራው በእንደዚህ ያለ ጋብቻ አይደለምን? ከብዙ ሕዝቦች መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም። እግዚአብሔርም ወዶት በሕዝቡ በእስራኤል ላይ አነገሠው፤ እርሱ ግን በባዕዳን ሴቶች አማካይነት ኃጢአት ሠራ። በዚህ ዐይነቱ ኃጢአት ላይ ወደቀ፤