ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቊጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።
1 ነገሥት 22:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚክያስም “በስተ ጓሮ በኩል ወዳለው ክፍል ሄደህ በምትሸሸግበት ጊዜ ታገኘዋለህ” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚክያስም፣ “ለመሸሸግ ወደ እልፍኝህ በምትሄድበት በዚያ ዕለት ታገኘዋለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚክያስም “በስተ ጓሮ በኩል ወዳለው ክፍል ሄደህ በምትሸሸግበት ጊዜ ታገኘዋለህ” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚክያስም፥ “እነሆ፥ በዚያ ቀን ልትሸሸግ ወደ ውስጠኛው እልፍኝህ በሄድህ ጊዜ ታያለህ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚክያስም “እነሆ፥ በዚያ ቀን ልትሸሸግ ወደ እልፍኝህ በሄድህ ጊዜ ታያለህ፤” አለ። |
ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቊጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።
“እንግዲህ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም ነቢያት የምለው ይህ ነው፦ ‘በምድሪቱ ሁሉ ላይ የክሕደትን መንፈስ ስላሠራጩ፥ መራራ ቅጠል እንዲበሉና መርዝ እንዲጠጡ አደርጋቸዋለሁ።’ ”
ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር እርሱንና ዘሮቹን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ከእንግዲህ ይህ ሰው በእናንተ መካከል የሚተርፍ ዘር አይኖረውም፤ እርሱ ራሱም ለሕዝቤ የማደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ለማየት የመኖር ተስፋ የለውም፤ ምክንያቱም እርሱ እናንተን በእኔ ላይ እንድታምፁ አድርጓችኋል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”
እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሐናምኤል ታስሬ ወዳለሁበት ወደ ዘብ ጠባቂዎች ክፍል መጥቶ “የመግዛት መብት ያንተ ስለ ሆነ መሬቴን ግዛ” አለኝ፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር እንደ ተናገረኝ ዐወቅሁ።
ስለዚህም አሜስያስ ሆይ! እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ ‘ሚስትህ በከተማይቱ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በጦርነት ይሞታሉ፤ ርስትህንም ባዕዳን በገመድ ለክተው ይከፋፈሉታል፤ አንተም በአሕዛብ ምድር ትሞታለህ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ያለ ጥርጥር ተማርከው ከአገራቸው ይወሰዳሉ።’ ”
ነገር ግን በቀድሞ ዘመን በሕዝቡ መካከል ሐሰተኞች ነቢያት እንደ ነበሩ፥ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር እንዲሠራጭ ያደርጋሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።