1 ዮሐንስ 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ልጅ ያለው ሕይወት አለው። የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ግን ሕይወት የለውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ግን ሕይወት የለውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። |
“እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማና በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እርሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ስለ ሆነ አይፈረድበትም።
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
እኔ ከክርስቶስ ጋር እንደ ተሰቀልኩ ያኽል ስለምቈጥር ከእንግዲህ ወዲህ ክርስቶስ በእኔ ውስጥ ይኖራል እንጂ እኔ ለራሴ ሕይወት የምኖር አይደለሁም፤ አሁንም በሥጋዊ አካሌ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ በማመን በተገኘው ሕይወት ነው።
በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የማይኖርና ከእርሱም ርቆ የሚሄድ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የለም፤ በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የሚኖር ሰው ግን አብና ወልድ ከእርሱ ጋር አሉ።