1 ዮሐንስ 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የምንፈጽም ከሆንን እርሱን የምናውቅ መሆናችንን በዚህ እናረጋግጣለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትእዛዞቹን ብንፈጽም እርሱን ማወቃችንን በዚህ ርግጠኞች እንሆናለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትእዛዛቱን ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን። |
“ብርሃን በጨለማ ውስጥ ይብራ!” ብሎ የተናገረ እግዚአብሔር በክርስቶስ መልክ የሚያበራውን የእግዚአብሔርን ክብር የማወቅ ብርሃን እንዲሰጠን ብርሃኑን በልባችን ውስጥ እንዲበራ አደረገ።
ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ ከቀሩት የእርስዋ ዘር ጋር ሊዋጋ ሄደ፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የሚጠብቁና ለኢየሱስ በታማኝነት የሚመሰክሩ ናቸው።