32 ብዙ ማስተዋልን ስለ ሰጠኸኝ፤ ትእዛዞችህን በትጋት እፈጽማለሁ።
32 ልቤን አስፍተህልኛልና፣ በትእዛዞችህ መንገድ እሮጣለሁ።
32 ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ፥ በትእዛዞችህ መንገድ ሮጥሁ።
እግዚአብሔር ለሰሎሞን እጅግ አስደናቂ የሆነ ጥበብንና አስተዋይነትን እንዲሁም ወሰን የማይገኝለትን ዕውቀት ሰጠው፤
እንደ ደመና በዙሪያችን የከበቡን እነዚህ ሁሉ ምስክሮች ስላሉን እኛ እንደ ሸክም የሆነብንን ነገር ሁሉ በእኛ ላይ የተጣበቀብንን ኃጢአት አስወግደን በፊታችንም ያለውን የሩጫ እሽቅድድም በትዕግሥት በመጽናት እንሩጥ።
ጌታ መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት ነጻነት አለ።
እናንተ በቆሮንቶስ የምትኖሩ ሰዎች ሆይ! እነሆ፥ በግልጥ ተናግረናችኋል፤ ልባችንንም በሰፊው ከፍተንላችኋል።
እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።”
ለተጨቈኑት መልካም ዜናን አበሥር ዘንድ፥ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩት ነጻነትን፥ ለታሰሩት መፈታትን ለማወጅ እግዚአብሔር ቀብቶ ስለ ላከኝ፥ የጌታ እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው።
ትእዛዝህን መፈጸም ስለምወድ በፍጹም ነጻነት እኖራለሁ።
መረማመጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
ስለዚህ ወልድ ነጻ ካወጣችሁ በእርግጥ ነጻ ትሆናላችሁ።
እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ሆናችሁ በነጻነት ኑሩ እንጂ ነጻነታችሁን የክፋት መሸፈኛ አታድርጉት።
ይህንንም አይተሽ ፈገግታሽ በደስታ ይፈካል፤ ከባሕር የሚገኘው በረከትና፥ ከሕዝቦች የሚመጣው ሀብት የአንቺ ስለሚሆን፥ ከደስታሽ ብዛት የተነሣ ልብሽ ይፈነድቃል።
በእግዚአብሔር ተማምነው የሚኖሩ ግን ኀይላቸው ይታደስላቸዋል። እንደ ንሥር በክንፍ ይበራሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ አይደክሙም።
እጄን ይዘህ ሳበኝ፤ አብረን እንሩጥ። ንጉሡ ወደ እልፍኙ አስገባኝ፤ በዚያም አብረን ደስ ይለናል፤ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ያስደስታል፤ ስለዚህ ቈነጃጅት ሁሉ እጅግ ያፈቅሩሃል።
ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈረ፤ በዚህኛው የውሃ ጒድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተነሣ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል፥ ያንን ቦታ ‘ረሖቦት’ ” ብሎ ሰየመው።