“መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቈጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥
1 ዮሐንስ 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናታልላለን። እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፤ እውነቱም በእኛ ውስጥ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ዘንድ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። |
“መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቈጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥
ኢሳይያስም “በቤተ መንግሥቱ ምን አዩ” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “ሁሉን ነገር አይተዋል፤ በግምጃ ቤቱ ካለው ሀብት ሁሉ ለእነርሱ ያላሳየኋቸው አንድም ነገር የለም” አለ።
“መቼም በደል የማይሠራ ሰው የለምና ሕዝብህ እስራኤላውያን ኃጢአት በመሥራት አንተን ቢያሳዝኑህ፥ አንተም ተቈጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ያ አገር ሩቅ ቢሆንም እንኳ፥
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።
ማንም ራሱን አያታል፤ በዚህ ዓለም የጥበብ ደረጃ ጥበበኛ መስሎ የሚታይ ቢኖር የእግዚአብሔርን እውነተኛ ጥበብ እንዲያገኝ ራሱን እንደ ሞኝ ይቊጠር።
አእምሮአቸው በረከሰና እውነት በጠፋባቸው ሰዎች የሚደረግ የማያቋርጥ ክርክርን ነው፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እግዚአብሔርን ማምለክ የሀብት ማግኛ ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል።
በደል ስለ ፈጸሙ ዋጋቸውን ይቀበላሉ፤ የእነርሱ ደስታ በጠራራ ፀሐይ መስከርና ያለ ቅጥ መፈንጠዝ ነው፤ በዚህ ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያቸው ከእናንተ ጋር በሚጋበዙበት ጊዜ አታላይ በሆነው ሥጋዊ ድርጊታቸው ነውረኞችና አሳፋሪዎች ናቸው።
ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት አለን” እያልን በጨለማ የምንኖር ከሆንን እንዋሻለን፤ በቃላችንም ሆነ በሥራችን እውነት የለም ማለት ነው።