1 ቆሮንቶስ 9:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር” ተብሎ በሕግ ተጽፎአል፤ ታዲያ እግዚአብሔር ይህን ያለው ስለ በሬዎች በማሰብ ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙሴ ሕግ፣ “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር” ተብሎ ተጽፏልና። ለመሆኑ፣ እግዚአብሔርን ያሳሰበው የበሬ ጕዳይ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፤” ተብሎ በሙሴ ሕግ ተጽፎአል። እግዚአብሔር ይህን ያለው ስለ በሬዎች በማሰብ ነውን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እህልህን በምታበራይበት ጊዜ የበሬውን አፉን አትሰረው።” እንግዲህ ይህን የጻፈ ለእግዚአብሔር በሬ አሳዝኖት ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕግስ ደግሞ ያን አይልምን? የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር ተብሎ በሙሴ ሕግ ተጽፎአልና። እግዚአብሔርስ ስለ በሬዎች ይገደዋልን? |
ነነዌ ክፉና ደጉን የማይለዩ ከአንድ መቶ ኻያ ሺህ ሕዝብ በላይ የሚኖሩባት ከተማ ነች፤ ብዙ እንስሶችም አሉባት፤ ታዲያ እኔ ለዚህች ታላቂቱ ከተማ አልራራምን?”
ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ምንም ዐይነት ሥራ አትሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ አገልጋዮችህም ልክ እንደ አንተው ዕረፍት ያድርጉ።