እነሆ፥ ለአንተ የሰማይ መንግሥትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆናል።”
1 ቆሮንቶስ 5:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በጌታችን በኢየሱስ ኀይል በመካከላችሁ በመንፈስ ስለምገኝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በመንፈስ ከእናንተ ጋራ ስለምሆን፣ በጌታችን በኢየሱስ ስምና በመካከላችሁ በሚገኘው በጌታችን በኢየሱስ ኀይል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር፥ በጌታችን ኢየሱስ ስም ተሰብስባችሁ፥ መንፈሴም አብሮችሁ ነው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተሰብስባችሁ፥ በእኔ ሥልጣን፥ በጌታችን በኢየሱስም ኀይል፥ |
እነሆ፥ ለአንተ የሰማይ መንግሥትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆናል።”
ይህንንም ብዙ ቀን እየደጋገመች ታደርግ ነበር፤ ጳውሎስ ግን ተበሳጨና ዞር ብሎ ርኩሱን መንፈስ “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከእርስዋ እንድትወጣ አዝሃለሁ!” አለው። ርኩሱም መንፈስ ወዲያውኑ ወጣ።
ይህን መልእክት ከእናንተ ርቄ ሳለሁ የጻፍኩላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ጌታም በሰጠኝ ሥልጣን አላስጨንቃችሁም፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ አይደለም።
እናንተ በእኔ ዐድሮ የሚናገረው ክርስቶስ መሆኑን ለማረጋገጥ ትፈልጋላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ የሚታየውም የእርሱ ኀይል ነው እንጂ ድካሙ አይደለም።
በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት፤ በእርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑ።
ወንድሞች ሆይ! ሥራ ፈት ከሆነውና ከእኛ በተላለፈላችሁ ትውፊት መሠረት ከማይኖር ክርስቲያን ሁሉ እንድትለዩ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።