Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 20:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እናንተ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ብትሉ ይቅር ይባልላቸዋል፤ እናንተ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ባትሉ ግን፥ ይቅር አይባልላቸውም” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ብትሉ፣ ኀጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል፤ ኀጢአታቸውን ይቅር ባትሉ ግን፣ ይቅር አይባልላቸውም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ኀጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ኀጢ​ኣ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ያላ​ች​ሁ​ላ​ቸው ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይቅር ያላ​ላ​ች​ኋ​ቸው ግን አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ውም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 20:23
11 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ለአንተ የሰማይ መንግሥትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆናል።”


“በእውነት እላችኋለሁ፤ በምድር የምታስሩት በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱትም በሰማይ የተፈታ ይሆናል።


ይህን ብሎ እፍ አለባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤


በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአት ይቅርታ እንደሚያገኝ ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል።”


ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤


በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በጌታችን በኢየሱስ ኀይል በመካከላችሁ በመንፈስ ስለምገኝ፥


በሐዋርያትና በነቢያትም መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑም ራስ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።


ከእነርሱ መካከል ሄሜኔዎስና እስክንድር ይገኛሉ፤ እነርሱ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ከመናገር መቈጠብን እንዲማሩ ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos