1 ቆሮንቶስ 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥራው በእሳት ተቃጥሎ የተደመሰሰበት ግንበኛ ግን ዋጋው ይቀርበታል፤ ይሁን እንጂ እርሱ ራሱ፥ በእሳት ውስጥ አልፎ ሳይቃጠል እንደሚቀር ሰው ይድናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥራው የተቃጠለበት ግን ሽልማት ይቀርበታል፤ እርሱ ራሱ ግን ይድናል፤ ይሁን እንጂ የሚድነው በእሳት ውስጥ በጭንቅ እንደሚያልፍ ሆኖ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፤ እርሱ ራሱ ግን ይድናል፤ ሆኖም ግን በእሳት አልፎ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥራው የተቃጠለበት ግን ዋጋውን ያጣል፤ እርሱም ከእሳት እንደሚድን ሰው ይድናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል። |
“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ደመሰስኩ ከእናንተም ብዙዎችን ደመሰስኩ፤ እናንተም የተረፋችሁት በእሳት ከተቀጣጠለ በኋላ ተነጥቆ እንደ ወጣ እንጨት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
የእግዚአብሔርም መልአክ ሰይጣንን “አንተ ሰይጣን! እግዚአብሔር ይገሥጽህ! ኢየሩሳሌምን የሚወድ እግዚአብሔር ይገሥጽህ! ይህ ሰው እኮ ከእሳት ውስጥ ተርፎ እንደ ወጣ እንጨት ነው” አለው።
ሰዎቹ ምንም ምግብ ሳይበሉ ብዙ ቀን ቈዩ፤ ስለዚህ ጳውሎስ በመካከላቸው ቆሞ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሰዎች! እኔ ያልኳችሁን ሰምታችሁ ከቀርጤስ ባትነሡ ኖሮ ይህ ሁሉ ጒዳትና ጥፋት ባልደረሰባችሁም ነበር።
አንዳንዶችን ከእሳት አውጥታችሁ አድኑአቸው፤ ለሌሎች በፍርሃት ራሩላቸው፤ ሆኖም በኃጢአት የረከሰውን ሰውነታቸውን የነካውን ልብስ እንኳ ሳይቀር ጥሉ።
ሀብታም ለመሆን በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥ የራቊትነትህን ኀፍረት ለመሸፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥ ለማየትም እንድችል የዐይን መድኃኒት ገዝተህ እንድትቀባ እመክርሃለሁ።