1 ቆሮንቶስ 11:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ኅብስት በምትበሉበትና ይህንንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን እንጀራ በምትበሉበት ጊዜ፣ ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ኅብስት በምትበሉበትና ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ኅብስት በምትበሉበት፥ ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታችን እስከሚመጣበት ቀን ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና። |
በዚህ ምክንያት በወንድሞች መካከል፥ “ይህ ደቀ መዝሙር አይሞትም” የሚል ወሬ ተሰራጨ፤ ነገር ግን ኢየሱስ፥ “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲኖር ብፈቅድ አንተ ምን አገባህ” አለ እንጂ፥ “አይሞትም” አላለም።
“እናንተ የገሊላ ሰዎች፥ ስለምን ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ቆማችኋል? ይህ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፥ ወደ ሰማይ ሲያርግ ባያችሁት ዐይነት ተመልሶ ይመጣል” አሉአቸው።
ይህም የሚሆነው ለእያንዳንዱ በየተራው ነው፤ ክርስቶስ ከሞት የመነሣት የመጀመሪያው ምሳሌ ነው፤ በኋላም ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ የእርሱ የሆኑት ከሞት ይነሣሉ።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
የትእዛዝ ድምፅ፥ የመላእክት አለቃ ድምፅ፥ የእግዚአብሔር እምቢልታም ይሰማል፤ ጌታ ራሱም በእነዚህ ታጅቦ ከሰማይ ይወርዳል፤ በክርስቶስ አምነው የሞቱትም አስቀድመው ይነሣሉ።
የሚቀጡትም በዚያን ቀን በቅዱሳኑ ሊከበርና በሚያምኑትም ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ በሚመጣበት ጊዜ ነው። እናንተም የእኛን ምስክርነት ተቀብላችሁ በማመናችሁ ከእነርሱ ጋር ትቈጠራላችሁ።
እንዲሁም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ አንድ ጊዜ ተሠውቶአል፤ ደግሞም ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን እርሱን የሚጠባበቁትን ለማዳን ሁለተኛ ጊዜ ይገለጣል።
የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ በድንገት ይመጣል፤ በዚያን ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ ፍጥረት ሁሉ በእሳት ተቃጥሎ ይጠፋል። ምድርና በእርስዋም ላይ ያለው ነገር ሁሉ ይቃጠላል፤
ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ ትውልድ የሆነው ሔኖክ ሲናገር እንዲህ ብሎአል፦ “እነሆ እግዚአብሔር እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክቱ ጋር ሆኖ በሁሉም ላይ ለመፍረድ ይመጣል፤
እነሆ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ሰው ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤ ይህ ነገር እውነት ነው፤ አሜን።