1 ቆሮንቶስ 10:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰዎች ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ከመጠን በላይ ሊፈነጥዙ ተነሡ” ተብሎ ስለ እነርሱ እንደ ተጻፈው፥ እነርሱ ጣዖትን እንዳመለኩ እናንተም እንደእነርሱ ጣዖትን አታምልኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቡ ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖት አምላኪዎች አትሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሕዝቡም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሕዛብ ተቀመጡ፤ ይበሉና ይጠጡም ጀመር፤ ሊዘፍኑም ተነሡ” ብሎ መጽሐፍ እንደ ተናገረ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንደ አመለኩ ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ። |
እርሱም የወርቅ ጒትቻውን ሁሉ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፤ የቀለጠውንም ወርቅ በቅርጽ መሥሪያ ውስጥ አግብቶ የወርቅ ጥጃ አድርጎ ሠራው። እነርሱም “እስራኤል ሆይ! ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላካችን ይህ ነው!” አሉ።
ይልቅስ ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብን አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ሳይታረድና ደሙም ሳይፈስ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምንም አትብሉ’ ብለን እንጻፍላቸው።
እኔ ግን የጻፍኩላችሁ ክርስቲያኖች ተብለው ከሚያመነዝሩ፥ ወይም ከሚስገበገቡ፥ ወይም ጣዖት ከሚያመልኩ፥ ወይም የሰውን ስም ከሚያጠፉ፥ ወይም ከሚሰክሩ፥ ወይም ከቀማኞች ጋር አትተባበሩ ብዬ ነው። እንደእነዚህ ካሉት ሰዎች ጋር፥ መብል አብራችሁ አትብሉ።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ ታውቁ የለምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖት አምላኪዎች፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥
ነገር ግን ይህን የሚያውቁ፥ ሁሉም አይደሉም፤ አንዳንዶች እስከ አሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ ሥጋን የሚበሉት ለጣዖት እንደ ተሠዋ አድርገው ነው፤ ስለዚህ ኅሊናቸው ደካማ በመሆኑ ይረክሳሉ።
“ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ ‘ፈጥነህ ከተራራው ራስ ላይ ውረድ፤ ከግብጽ ምድር መርተህ ያወጣኸው ሕዝብህ፥ ክፉ ነገር በማድረግ ረክሶአል፤ እኔ ከሰጠኋቸው ትእዛዝ ሁሉ ወዲያውኑ ርቀው፥ የሚያመልኩትን ጣዖት ለራሳቸው ሠርተዋል።’