Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 10:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “ሕዝቡም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ሕዝቡ ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖት አምላኪዎች አትሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ሰዎች ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ከመጠን በላይ ሊፈነጥዙ ተነሡ” ተብሎ ስለ እነርሱ እንደ ተጻፈው፥ እነርሱ ጣዖትን እንዳመለኩ እናንተም እንደእነርሱ ጣዖትን አታምልኩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “አሕ​ዛብ ተቀ​መጡ፤ ይበ​ሉና ይጠ​ጡም ጀመር፤ ሊዘ​ፍ​ኑም ተነሡ” ብሎ መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶቹ እንደ አመ​ለኩ ጣዖ​ትን የም​ታ​መ​ልኩ አት​ሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 10:7
14 Referencias Cruzadas  

ኢያሱ የሕዝቡን የጩኸት ድምፅ በሰማ ጊዜ ሙሴን፦ “የጦርነት ድምፅ በሰፈሩ ውስጥ አለ” አለው።


እንዲህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃውንና ዘፈኑን አየ፤ የሙሴ ቁጣ ነደደ፥ ጽላቶቹን ከእጁ ወርውሮ ከተራራው በታች ሰበራቸው።


ከእጃቸው ተቀብሎ በቅርጽ መሥሪያ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃ አደረገው፤ እርሱም፦ “እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው” አላቸው።


ነገር ግን ከጣዖት ርኩሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቆርጣለሁ።


ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ።


አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ስግብግብ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ።


ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥


ነገር ግን ይህ ዕውቀት በሁሉ ዘንድ አይገኝም፤ አንዳንዶች ግን ጣዖትን እስከ አሁን ድረስ ስለ ለመዱ፥ ለጣዖት የተሠዋ ነው፤ ብለው ይበላሉና፥ ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።


“ከዚያም ጌታ፥ ‘ተነሥ፥ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ፥ ከግብጽ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ክፉ ነገር በማድረግ ረክሰዋል፤ ፈጥነው ካዘዝኋቸው መንገድ ፈቀቅ ብለዋል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሳቸው ሠርተዋል’ አለኝ።


ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos