ዘካርያስ 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዐይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን የወጓትን አሕዛብ ሁሉ የሚመታበት መቅሠፍት ይህ ነው፤ ገና በእግራቸው ቆመው ሳሉ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዐይኖቻቸው በጕድጓዶቻቸው ውስጥ እንዳሉ ይበሰብሳሉ፤ ምላሶቻቸውም በአፎቻቸው ውስጥ እንዳሉ ይበሰብሳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሩሳሌምን ለመውጋት በሚነሣሡ ሕዝቦች ላይ እግዚአብሔር ቀሣፊ በሽታ ያመጣባቸዋል፤ በሕይወት እያሉ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዐይናቸው በዐይነስባቸው ውስጥ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፣ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፥ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። |
እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሃትን፥ ነፍስን የሚያኮስስና ዓይንን የሚያፈዝዝ ክሳትና ትኩሳት አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ይበሉታልና ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።
በፈረሶች፥ በበቅሎዎች፥ በግመሎች፥ በአህዮች፥ እንዲሁም በዚያም ሰፈር ባሉ እንስሶች ሁሉ ላይ በሰዎች ላይ እንደ ሆነው ዓይነት ቸነፈር በእነርሱም ላይ ይሆናል።
እኔም፦ “እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” አልኩት። እርሱም፦ “አንድ ሰው ራሱን ቀና ማድረግ እስኪሳነው ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፤ እነዚህ ግን ሊያስፈራሯቸው፥ የይሁዳንም አገር ለመበተን ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊቆርጡ መጥተዋል” ብሎ ተናገረ።
ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ይበዘብዟታል፥ ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።