Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 21:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አንተም ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀትህ በየዕለቱ እስኪ ወጣ ድረስ በክፉ የአንጀት ደዌ ትያዛለህ።’ ”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አንተም ራስህ በየዕለቱ እየባሰ በሚሄድ የአንጀት በሽታ ክፉኛ ትታመማለህ፤ በመጨረሻም ሕመሙ አንጀትህን ወደ ውጭ ያወጣዋል።’ ”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አንተም ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀትህ እስኪወጣ ድረስ በማይድን ክፉ የአንጀት በሽታ ትሠቃያለህ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አን​ተም ከደ​ዌው ጽናት የተ​ነሣ አን​ጀ​ትህ በየ​ዕ​ለቱ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ በክፉ የአ​ን​ጀት ደዌ ትታ​መ​ማ​ለህ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አንተም ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀትህ በየዕለቱ እስኪወጣ ድረስ በክፉ የአንጀት ደዌ ትታመማለህ።”

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 21:15
11 Referencias Cruzadas  

ይህም ሰው በዐመፅ ዋጋ መሬት ገዛ፤ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤


መራገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥ እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች።


ልብህ በፍርሀት ከመሞላቱና ዐይንህ ከሚያየው የተነሣ፥ ሲነጋ፥ ‘ይመሽ ይሆን?’ ሲመሽ ደግሞ፥ ‘ይነጋ ይሆን?’ ትላለህ።


በተጨማሪም ጌታ በዚህ የሕግ መጽሐፍ ያልተጻፈውን ማንኛውንም በሽታና መከራ እስክትጠፋ ድረስ ያመጣብሃል።


ጌታ አስፈሪ መቅሠፍት፥ አስጨንቆህ የሚቆይ መዓት መቅሠፍት፥ አሠቃቂና ጽኑ በሽታ በአንተና በዘሮችህ ላይ ይልክባችኋል።


ጌታ እንድትገባ በሚያደርግበት ምድር ለአሕዛብ ሁሉ ድንጋጤ፥ መቀለጃና መዘባበቻ ትሆናለህ።


በማትድንበት በግብጽ ብጉንጅ፥ በእባጭ፥ በሚመግል ቁስልና በዕከክ ጌታ ያሠቃይሃል።


ውኃውንም እንድትጠጣ ካደረጋት በኋላ እንዲህ ትሆናለች፤ የረከሰች ብትሆንና ለባልዋ ፍጹም ታማኝ ባትሆን፥ እርግማንን የሚያመጣው ውኃ ገብቶ መራራ ሥቃይ ያመጣባታል፥ ሆድዋም ይነፋል፥ ጭንዋም ይሰለስላል፤ ሴቲቱም በሕዝብዋ መካከል ለመርገም ትሆናለች።


ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያንጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።


እነሆ፥ ጌታ ሕዝብህንና ልጆችህን ሚስቶችህንም ያለህንም ሁሉ በታላቅ መቅሰፍት ይቀስፋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios